እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:25:27 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ18ነጥብ 5ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል

1 ደቂቃ ንባብ
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ18ነጥብ 5ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል
ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ በማኑዋልና በዲጂታል አማራጮች ባከናወነው ምዝገባ 10ሚሊዮን 133ሺህ 639 ወንዶችና 8ሚሊዮን 422 ሺህ 698ሴቶች ተመዝግበዋል።
ዘንድሮ ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 
ከ18ነጥብ 5ሚሊዮን ዜጎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ለምርጫን የመራጮች ምዝገባ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ከየካቲት 28 ቀን 2018 ጅምር በመካሄድ ላይ ነው።

በመጀመሪያው ሣምንት ለምርጫው የተመዝገቡት ዘጠኝ ሚሊዮን ዜጎች ነበሩ፡፡

የምርጫው ሁለተኛ ሣምንት ምዝገባ ሳይጠናቀቅ የመራጮች ቁጥር ከመጀመሪያው ሣምንት ያልተናነሰ መጨመሩን የቦርዱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ቦርዱ እስከ መጋቢት 10/2018 በማኑዋልና በዲጂታል አማራጮች ባከናወነው ምዝገባ 10ሚሊዮን 133ሺህ 639 ወንዶችና 8ሚሊዮን 422 ሺህ 698ሴቶች ተመዝግበዋል።

ከተመዝጋቢዎቹ 54 ነጥብ 3በመቶ ያህል ወንዶች ሲሆኑ፤ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡

የመራጮች ምዝገባው የተከናወነው በ47ሺህ 657 ምርጫ ጣቢያዎች እንደሆነም አስረድቷል።

በምዝገባ ላይ ካሉት ጣቢያዎች መካከል 215ቱ ጣቢያዎች በመራጭነት መመዝገብ ያለባቸውን ቁጥር በማለፋቸው ንዑስ ጣቢያዎች መከፈታቸውን አመልክቷል።

ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሠለጠናቸውን 187ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰማራቱን ገልጿል።

ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የሚደረገው የመራጮች ምዝገባ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ድረስ ይቀጥላል፡፡



ምርጫምርጫ ቦርድምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!