እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:14:27 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

ለወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠረው የግብርና ኢንተርፕራይዝ

1 ደቂቃ ንባብ
ለወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠረው የግብርና ኢንተርፕራይዝ
ይህ 214 ሥራ አጥ ወጣቶችን ያደራጀ ተቋም ፎሶሊያ፣ አተርና ብሮክሊን በማልማት ላይ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል።
1 / 2

በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክፍለ ከተማ በኪሌሎ ወረዳ ባለፈው ዓመት ነው የተመሠረተው።

ስሙ የቡራ ባሩ የመስኖ ሥራ ኢንተርፕራይዝ ይባላል።

ይህ 214 ሥራ አጥ ወጣቶችን ያደራጀ ተቋም ፎሶሊያ፣ አተርና ብሮክሊን በማልማት ላይ ነው፡፡ 
    
ኢንተርፕራይዙ ባለፈው ዓመት በ43 ሄክታር መሬት ላይ ከአንድ ሺህ ኩንታል በላይ ፎሶሊያ፣ 2ሺህ395 ኩንታል አተርና 877 ኩንታል ብሮክሊን አምርቷል።

በልማቱም  4 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ማትረፍ ችሏል ይላል የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ፡፡ 

 ምርቱን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት ባለፈ፤ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገተ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ 

ኢንተርፕራይዙ ከአባላቱ ባለፈ በአጨዳ ወቅት 500 ለሚሆኑ ሰዎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአንድ ሰው በቀን እስከ 500 ብር ይከፍላል፡፡  
      
መንግሥት ለኢንተርፕራይዙ 78 ሄክታር መሬት በመስጠት፣ ለመስኖ አገልግሎት  የሚውል ውሃ በማውጣት፣ ለምርቱ የገበያ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ድጋፍ  ማድረጉንም አስታውቋል፡፡ 
  
የኢንተርፕራይዙ ሊቀመንበር ወጣት አባይ ታደሰ በሕንፃ ኤሌክትሪክ ዝርጋታ ሙያ በዲፕሎማ ተመርቆ ለሰድስት ዓመታት ሥራ አጥ ሆኖ እንደቆየ ያስታውሳል፡፡ 

ሥራ አጥ ወጣቶች ቅጥርን ከመጠበቅ ይልቅ ተደራጅተው በግብርና ልማት ላይ ቢሰማሩ የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙም መክሯል፡፡ 

ይሄን ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቤተሰቡን በአግባቡ ማስተዳደር ይቸግረው እንደነበር ገልጾ ፣ በአሁኑ ወቅት በወር ስምንት ሺህ ብር ደሞዝ እያገኘ ኑሮውን በመምራት ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡    

በቀጣይም ኢንተርፕራዙን በማጠናከር ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራ መሆኑንም ሊቀመንበሩ አመላክቷል፡፡  


ኢኮኖሚወጣቶችሥራ ፈጠራግብርና

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!