እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:51:50 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊቀነስ ነው

1 ደቂቃ ንባብ
ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊቀነስ ነው
አዲሱ የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና በየዓመቱ የሚደረግ ሲሆን፥ የመጀመሪያውን ውድድር ግሪክ እንድታዘጋጅ መመረጧን የድርጅቱ መግለጫ አመልክቷል፡፡
ኢትዮጵያን በዓለም አትሌቲክስ ውድድሮች ካሳወቋት ውደድሮች አንዱ ማራቶን ነው።

ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ዓለምን  ያሰደመመው ይህንን ረጅሙን ሩጫ በማሸነፉ ነበር።

ከአራት ዓመታት በቶኪያ  ይህንን 42ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ርቀት ለሁለተኛ ጊዜ በዓለም ገናና የሆነው በማራቶን አሸንፎ ነው።

አትሌት ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ኦሎምፒክ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሆና የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው በዚህ ረጅም ርቀት ተወዳድራ አሸንፋ ባገኘችው ውጤት ነው።

ከኃይሌ  ገብረ ሥላሴ እስከ ታምራት ቶላ፤ከአሰለፈች መኩሪያ እስከ ቲኪ ገላና ያሉት ኢትዮጵያውያን ማራቶንን ሮጠው ድል አስመዝግበዋል።

የዓለምን አትሌቲክስን ወድድሮች የሚያዘጋጀው አካል ከአራት ዓመታት በኋላ በሚያዘጋጃቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ላይ ማራቶንን እንደማያካትት ያመላከትበት መግለጫ አውጥቷል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2030 ጀምሮ ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ውጪ ይሆናል ብሏል፡፡

ነገር ግን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027ና በ2029 በሚካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎቾ  የውድድሩ አካል ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ከዚያ በኋላ ግን ማራቶን የሚስተናገድበት  አዲስ ዓመታዊ የአትሌቲክስ ውድድር እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል፡፡

በዚህም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2030 የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና የሚል ራሱን የቻለ ውድድር ይጀምራል፡፡

አዲሱ የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና በየዓመቱ የሚደረግ ሲሆን፥ የመጀመሪያውን ውድድር ግሪክ እንድታዘጋጅ መመረጧን የድርጅቱ መግለጫ አመልክቷል፡፡
ስፖርትአትሌቲክስማራቶን

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!