እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:24:58 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

ምስጢራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራትዎ በፊት ቢያውቋቸው

1 ደቂቃ ንባብ
ምስጢራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራትዎ በፊት ቢያውቋቸው
ምስጢራዊ መረጃዎን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intellegence)ከማጋራትዎ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮቾ አሉ።

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት ሥራችንን እጅግ እያቀለለልን ቢሆንም፣ ከዕድገቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶች ግን አልቆሙም።

በቅርቡ በChatGPT የሶፍትዌር ሥርዓት ላይ በተገኘ ከፍተኛ የደህንነት ክፍተት፣ ጥቃት አድራሾች በአንድ "አደገኛና አጥፊ ትእዛዝ" (Malicious Prompt) ብቻ የግልና የተቋማትን መረጃዎች መዝረፍ የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጥሮ እንደነበር የቼክ ፖይንት (Check Point) ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል።

ይህን የደህንነት ስጋት፣ አጥፊ የሆኑ የጽሁፍ ትዕዛዞችን በመጠቀም የChatGPTን የመከላከያ አጥር በመጣስ፣ምስጢራዊ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች ሰርቨር (Server)ማስተላለፍ ያስችላል።

ይህም ተጠቃሚዎች ወደ ሰው ሰራሸ አስተውሎት የሚጭኗቸውን ፋይሎች፣ የግል መልዕክቶችና ምሥጢራዊ የድርጅት ሰነዶች ለከፍተኛ አደጋ አጋልጦ ቆይቷል።

ራስዎን እንዴት ይጠብቁ?

ትዕዛዞችን (Prompts) ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፥

በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ "ምርጥ ውጤት ያስገኛሉ" ተብለው የሚሰራጩ የትዕዛዝ ዓይነቶችን ሳያረጋግጡ አይጠቀሙ።

 እነዚህ ትዕዛዞች መረጃዎን በድብቅ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች የሚልኩ ድብቅ መመሪያዎችን ሊይዙ ይችላሉ።

ምስጢራዊ ፋይሎችን ከመጫን ይቆጠቡ፥

የባንክ መረጃዎችን፣ የጤና ሰነዶችን ወይም የተቋማትን ምሥጢራዊ ፋይሎች ወደ ሰው ሰራሽ ሲስተሞችን ከመጫንዎ በፊት በደንብ ያስቡ ይላል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘው መረጃ። 

ሰው ሰራሽ አስተውሎት መረጃውን ለሌላ ወገን እያጋራ መሆኑን ራሱ እንኳ ላያውቀው እንደሚችል ልብ ሊባል ይገባል።

ምንጊዜም ንቁ ይሁኑ፦

ምንም እንኳን ለChatGPT የደህንነት ማስተካከያ ቢደረግለትም፣ አጥቂዎች አዳዲስ የጥቃት ዘዴዎችን መፈለጋቸውን አያቆሙም። ስለዚህ ከማይታወቁ ምንጮች የሚመጡ "አቋራጭ መንገዶችን" ሁልጊዜም በጥርጣሬ ይመልከቱ።


ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂሳይንስና ቴክኖሎጂ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!