እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:29:16 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ፋታ ይሰጣታል

2 ደቂቃ ንባብ
 ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ፋታ ይሰጣታል
ኢትዮጵያ ከውጭ ነዳጅ ገዝታ የምታስገባ አገር በመሆኗ የነዳጅ አቅርቦቷ በግማሽ ቀንሶባት ነበር።በአዲስ አበባ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሰልፍ ይዘው ወረፋ ጠብቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የነዳጅ ሰልፎች ተመልክተናል።ለኢትዮጵያ የግብይት ተዋንያንና መንግሥት ፋታ በሚሰጥ መልኩ አሜሪካ፣እሥራኤልና ኢራን ያደረጉት ስምምነት አድርገዋል።

ፋላሚዎቹ አገሮች  ለ14 ቀናት ያደረጉት ተኩስ አቁም በጊዜያዊነትም ቢሆን ኦፎይታ የሚሰጥ ነው።

ማክሰኞ ሌሊት የተደረሰው ስምምነት ፓኪስታንና ኦማን ባደረጉት ዲፕሎማሲያዊ  ጥረትና ጫና ወታደራዊ ዝግጅትንና ፍጥጫን አስቁሟል።የኢራንን የሲቪል መሠረተ ልማትን ለማፈራረስና የዓለም የኢነርጂ ግብይትን በቀውስ ውሰጥ ከመቆየት ታድጎታል።

ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተፋላሚዎቹ አገሮች በዲፕሎማሲው መስክ የተደረገው ስምምነት ሌሎች አገሮች ያደረጉት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያደረጉት ነውና እምብዛም ስሜት ላይሰጠው ይችላል።ካለፈው ወር ወዲህ ከአዲስ አበባ እስከ ሐዋሳ  የተፈጠረውን የኑሮ ውድነትና የከተሞች እንቅስቃሴ መዳከም መንስዔ መሆኑ ግን ሕይወቱን ይነካዋል።

ጉዳዩ  የዓለም አንድ አምስተኛ ነዳጅ  ማስተላለፊያው የሆርሙዝ ሰርጥን በፍጥነትና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ አገልግሎት አንዲሰጥ መልሶ መክፈት በመሆኑ ነው።

ጦርነቱ በተፋፋመበት ወቅት የተዘጋው መሥመር 95በመቶ የሚሆኑ መርከቦች እንዳይንቀሳቀሱ በማድረጉ የዓለም ነዳጅ ዋጋ እንዲንር አድርጓል።

ኢትዮጵያ ከውጭ ነዳጅ ገዝታ የምታስገባ አገር በመሆኗ የነዳጅ አቅርቦቷ በግማሽ ቀንሶባት ነበር።በአዲስ አበባ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሰልፍ ይዘው ወረፋ ጠብቀዋል።

ስሞምነቱ ወደ አገር ውስጥ ሳይገባ የቀረውን ከ180ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ለማስገባት ያስችላል ተብሎም ይጠበቃል። ይህም በነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች የሚታዩትን ሰልፎች ያሰቀራል።የቤንዚንና የጋዝ አቅርቦትን ያሻሽለዋል።

በተጨማሪም የዋጋ ንረትን በማርገብ ኑሮን ለማረጋጋት ያስችላል በማለትም የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አስረድተዋል።

 የትራንስፖርት ዋጋም እየተረጋጋ ስለሚሄድ የግብርና ምርቶች አቅርቦትን በማሻሻል በከተሞች የዋጋ ቅናሽ ሊያመጣ እንደሚችልም ይጠበቃል።

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስምምነቱ የተረጋጋ የዓለም ገበያ መፈጠሩ የአገሪቱን የመጠባበቂያ ክምችትና የብርን የመግዛት አቅም ከመቀነስ እንደሚታደገው  ያለውን ተስፋ ገልጿል።

በአቪዬሽን ዘርፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሁለት ሣምንታት በሚቆየው ተኩስ አቁም ስምምነት ተጠቃሚ ከሚያደርጋቸው መካከል ነው።በየሣምንቱ 137ነጥብ 5ሚሊዮን ዶላር ገቢ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በሚያደርጋቸው 10 በረራዎች ሲያጣና የጦርነት ቀጣናውን ለማለፍ ረጃጅም በረራዎች ሲያደርግ ነበር።

ስምምነቱ በአፍሪካ፣በእስያና በአውሮፓ መካከል በሚያደርጋቸው በረራዎች ይጫወት የነበረውን የአገናኝነት ሚና ዳግም ለመመለስ ያስችለዋል ተብሎም ይገመታል።

የአገሪቱ የወጪ የሆኑ ምርቶችን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለማድረስም ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል።

ኢትዮጵያውያን ለሁለት ሣምንታት የተደረሰው ስምምነት ዘላቂ እንዲሆንና የአፍሪካ ቀንድ አገሮችን ኢኮኖሚ ተስፋ እንዲያለመልም ይመኛሉ።




 







የነዳጅ አቅርቦትኢኮኖሚ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!