እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:13:31 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ባህልና ኪነ-ጥበባት

ሹዋሊድ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል

2 ደቂቃ ንባብ
ሹዋሊድ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል
በዓሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ የአብሮነት እሴትን እያጎለበቱ ከሚገኙ ባህላዊ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በተለይም በምሥራቁ የአገሪቱን ክፍል የባህል ትውውቅ በመፍጠር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር በማጠናከር በኩልም ገንቢ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል ።

በመላው ዓለም የሚገኙ የእስልምና እምነት በየዓመቱ ለአንድ ወር ይፆማሉ።ፆሙን የሚያደርጉበት ወር  ረመዳን ይባላል። 


የፆሙ ወር ሲያበቃ ደግሞ የኢድ አል ፈጥር በዓል ይከበራል።የዘንድሮውን በዓል ባለፈው ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 አክብረውናል።


በሐረሪ ብሔረሰብ ከፆሙም ከበዓሉ የተሻገረ በዓል አለ።የሹዋሊድ የሚባል።


በዓሉ የረመዳን የፆም ወቅት አብቅቶ የኢድ አል ፈጥር ከተከበረ በኋላ ለሰድስት ቀናት ተፁሞ የሚከበር ነው።

በዓሉ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጆችን ከአገር ውስጥና ከውጭ ያሰባሰባል።


በተጨማሪም የብሔረሰቡ ተወላጅ ያልሆኑ ሰዎችን ከመላው አገሪቱ፣ቱሪስቶችንና ሌሎች በዓሉን ለማክበር የሚፈልጉ ሰዎችን አካቶ ይከበራል።


ሹዋሊድ በሐረር በዚህ ሣምንት ነው የሚከበረው።ለመሆኑ ዝግጅቱ ምን ይመስላል?


የሹዋሊድ ክብረ በዓል ሰላምን፣ አብሮነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ እንደሚከበር የሐረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።


ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ የሹዋሊድ ክብረ በዓል በሐረሪ ብሔረሰብ ዘንድ ለምዕተ ዓመታት ሲከበር የኖረና በትውልድ ቅብብሎሽ ባህሉንና ወጉን ጠብቆ ከነክብሩ የደረሰ ባህላዊ በዓል መሆኑን አመልክቷል።


የሐረሪ ሕዝብ ልዩ መገለጫ እሴት የሆነው በዓል ከበዓልነቱ ባሻገር፤ የሐረሪ ሕዝብ ጥልቅ የሆነ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እሴቶች መገለጫ ነው ብሏል።


በዓሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ የአብሮነት እሴትን እያጎለበቱ ከሚገኙ ባህላዊ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በተለይም በምሥራቁ የአገሪቱን ክፍል የባህል ትውውቅ በመፍጠር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር በማጠናከር በኩልም ገንቢ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል ።


በዓሉ የሐረሪ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፤ የመላ ኢትዮጵያውያን ከዚያም አልፎ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ሃብት ሆኖ እንደሚገኝ አመልክቷል።


ሹዋሊድ በተለይም የክልሉን ብሎም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ እንዲጎለብት ከማድረግ አንፃር የላቀ ጠቀሜታ ያለው በዓል ነው።


የዘንድሮው በዓል "ሹዋሊድ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ለቱሪዝም እድገታችን" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።


የዘንድሮው የሹዋሊድ በዓል አከባበርም ሰላምን፣ አብሮነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።


በበዓሉም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችና አጎራባች ክልሎች በሐረር ከተማ የባህል፣ ፌሲቲቫልና ዐውደ ርዕይ፣ የልማት ሥራዎች ጉብኝትን ጨምሮ ሌሎች መርሃ ግብሮች ይካሄዱበታል። 


በበዓሉ ላይም ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶች ይታደሙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጽህፈት ቤቱ ጠቁሟል።


ሹዋሊድ ከኅዳር 25 ቀን 2016 ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ በዓል ነው።


የሹዋሊድ በዓልበዓል

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!