
የዘንድሮው አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዓት መመዝገቢያ ማሽን ታግዞ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ 55ኛው ሻምፒዮና በቀጣዩ ሣምንት በአዲስ አበባ አደይ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
ከመጋቢት 15 እስከ 20 ቀን 2018 በሚደረገው ከአንድ ሺህ በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ ተገልጧል፡፡
በሻምፒዮናው የሚሳተፉት የዘጠኝ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮችን ጨምሮ ከ36 ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች ናቸው፡፡
በውድድሩ ለሚያሸንፉት አትሌቶች የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በምታስተናግደው ዓለም አቀፍ ውድድር እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡
በሻምፒዮናው የሰዓት መመዝገቢያ ማሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡
በሻምፒዮናው በሚደረጉ ውድድሮች የሚመዘገቡ ሰዓቶች ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን እንደሚያገኙ ም ለመረዳት ተችሏል፡፡
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!