እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:23:38 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

በሣምንት አንድ ሚሊዮን ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው

2 ደቂቃ ንባብ
በሣምንት አንድ ሚሊዮን ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገቡ ነው
አሁን በሣምንት አንድ ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት የሚመዝገቡበት ጊዜ ላይ ተደርሷል፡፡

ኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ባለቤት ለማድረግ እየሰራች መሆኗ ይታወቃል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት ይህን ብሔራዊ መታወቂያ አውጥቶ ለመጠቀም የነበረው ፍላጎት ዝቅተኛ በመሆኑ መታወቂያ ካርዱን የወሰዱት ዜጎች ቁጥር አናሳ ነበር፡፡

አያደር መታወቂያውን ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር እየተሳሰረ በመምጣቱ ዜጎች መታወቂያ ካርዱን ለማግኘት ያላቸውን ፍላጎት እያደገ መጥቷል፡፡

በዚህም በሣምንት አንድ ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት በመመዝገብ ላይ እንደሚገኙ ነው የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የሚገልጸው፡፡

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላትና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ እንደተናገሩት፤ በፕሮግራሙ እስካሁን 38 ሚሊዮን ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ወስደዋል፡፡

የባንክ ደንበኞች የሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የምዝገባ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ሁሉም ባንኮች ደንበኞቻቸው በቅርንጫፎችና በኦንላይን አገልግሎት የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ ማድረጋቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ፋይዳ መታወቂያ ለባንኮች ያለው ፋይዳ የላቀ በመሆኑ  ከሁለት ሺህ በላይ የመመዝገቢያ ማሽኖችን ገዝተው ምዘገባውነ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ በማመላከት፡፡

በባንኮች በሌሎች ተቋማት 80 ሚሊዮን ደንበኞችን መረጃ ለማረጋገጥ መሰራቱን የገለጹት አቶ ሳሚናስ ባንኮች ብቻ በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ደንበኞችን መረጃ እያረጋገጡ ናቸው  ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ምዝገባው በባንኮች፣ በኢትዮ ቴሌኮምና በኢትዮ ፖስታ አማካይነት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

በተቋማቱ አምስት ሺህ የምዝገባ ማሽኖች ያህል መኖራቸውን ገልጸው፣ በቅርቡ ተጨማሪ ሦስት ሺህ ማሽኖች ወደ ምዝገባ ይገባሉ ብለዋል፡፡

በቅርቡ በሱፐር አፕ ኤጀንት በኩል በገጠር አካባቢዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ እንደሚጀመር አመልክተዋል፡፡

ዲጂታል መታወቂያፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!