እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:26:33 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የከተሞች የግብርና ልማት ይፋ ተደረገ

3 ደቂቃ ንባብ
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የከተሞች የግብርና ልማት ይፋ ተደረገ
ፍኖተ ካርታው ጥብቅ የቴክኖሎጂ ትስስር ለከተማ ግብርና ያስቀምጣል፡፡መንግሥት እንደ አውሮፓውን አቆጣጠር 2035 ቢያንስ 10 በመቶ የከተማ ግብርና ማሳዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዞ ለማካሄድ አቅዷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የከተማ ግብርናን በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሚያስፋፋበትን ዕቅድ ማዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ዕቅዱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2035 ድረስ የሚከናወን ፍኖተ ካርታም አለው፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የሚመራውና እንደ ዲጂታል ግሪን ያሉ አጋሮችን የሚያቀናጀው ዕቅድ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፉ መሣሪያዎችን ለከተማ ግብርና አልሚዎች ያስተዋውቃል፡፡

ይህም የግብርና ኤክስቴንሸን ባለሙያዎችን እጥረት ለመታደግ ያስችላል ተብሎም ታምኖበታል፡፡

በዕቅዱ መሠረት ባለሙያዎቹ የሰው ሰራሸ አስተወሎት አገልግሎትን በአገር ውስጥ ቋንቋዎችና በድምጽና በጽሁፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

የቴክኖሎጂው ባለሙያዎች ለአልሚዎቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ፤ የሙያ ምክር ይለግሳሉ፡፡ ከዚያም አልፎ በሰብል ላይ የሚከሰቱ በሸታዎችንም ያክማሉ ይላል መረጃው፡፡

አልሚዎቹ በሸታ የታየባቸወን ተክሎች ፎቶ አንስተው ለሰው ሰራሸ አስተውሎት ሲያቀርቡ መታከም የሚችሉበትን መንገዶች በመጠቆም መፍትሄ ይሰጣቸዋል በማለትም ያብራራል፡፡

ቴክኖሎጂው በከተሞች የግብርና ልማትን በፍጥነት በማስፋፋት እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የከተማ ግብርና ልማት በልጦ እንደሚከናወን ባለሙያዎች አስረድተዋል፡፡

የቴክኖሎጂው ብቃትና ተፈላጊነትም አዳጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ፍኖተ ካርታው ቴክኖሎጂው ከከተማ ግብርና ልማት ጋር ጥብቅ ትስስር እንደሚኖረውና መንግሥት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆኑት የከተማ ግብርና ማሳዎች ሙሉ በሙሉ በስው ሰራሽ አስተውሎት ይከናወናሉ ብሏል መረጃው ፡፡

ማሳ በሮቦቶች የሚከናወኑ ድርብርብ ግብርና (Vertical Farming) በማሳዎቹ የሚያካተት ሲሆን፣ ለማሳዎቹ የሚያስፈልጉ ነገሮች በራሳቸው በማዘጋጀትና የአበቃቀል ሂደታቸውን በመከተታተል መረጃ ይይዛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰው ሰራሸ አስተዉሎት በድሮን የተደገፈ  ቁጥጥር ከአየር ላይ ያደርጋል፡፡

ቴክኖሎጂው ተክሎች የወሃ አጠቃቀም ችግር ሲያጋጥማቸውና በበሸታ ሲጠቁ ከአልሚዎቹ ቀድሞ በማወቅ የሚያክም መሆኑንም ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡

ሌላወ በአገሪቱ ብሔራዊ ዲጂታል ግብርና መሠረተ ልማት ቁልፍ የልማት ምሰሶ የሚሆነው ‹‹ኦፕን አግሪ ኔት›› ተበሎ የሚጠራው ነው፡፡ መድረኩ ሰው ሰራሽ አስተወሎትን ተጠቅሞ የገበያ አዝማሚያዎችን ይገመገማል፤ አልሚዎቹ ምን ዓይነት ሰብል ማልማት እንዳለባቸውም ይጠቁማል፡፡

ይህም በገበታ ላይ ተፈላጊ ምርቶችን አምርተው ለአዲስ አበባ ገበያ በማቅረብ በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ውሳኔ ለመወሰን እንደሚያስችላቸው ተመላክቷል፡፡

ቴክኖሎጂው በትኩሱ ወደ ገበያ መቅረብ ያለባቸው ምርቶች በተለይ አትክልትና ፍራፍሬ በአቅርቦት ሰንሰለትና ድኀረ ምርት ችግሮች ይገጥማቸዋል፡፡

ባለሙያዎች እንደሚያቀርቡት ግምት ከሆነ፤ 40 በመቶ የሚሆነው ፈጥነው ለገበያ መቅረብ ያለባቸው ምርቶች ለተጠቃሚው ከመድረሳቸው በፊት ይበላሻሉ፡፡

አቅርቦቱ በሰው ሰራሸ አስተውሎት በመጠቀም እንዲሳለጥና ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ማጓጓዣዎች በመጠቀም የከተማ ግብርና ማሳዎችን ከንግድ ማዕከላት በማገናኘት ለመፍታት እንደታቀደ ከመረጃው መመልከት ተችሏል፡፡

ፍኖተ ካርታው የቆሻሻ አወጋገድን ከከተማ ግብርና ሥነ ምህዳር በማገናኘት ሚና እንዳለውም ተመላክቷል፡፡ መንግሥት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ቆሻሻን ለከተማ ግብርና ልማት ለማዋል እንደሚረዳ አሳይቷል፡፡

ቴክኖሎጂው ተረፈ ምርት የሚገኝባቸውን ቦታዎችን መለየት፣ ብቃት ያለው የአሰባሰብና የአቅርቦት መንገዶች ተጠቅሞ ከተረፈምርቱ ጠቃሚ የግብርና ግብዓቶች ማምረት እንደሚቻልም አመላክቷል፡፡

በዕቅዱ የተቀመጠው ሌላው ነገር  ከጥቁር ወታደር ዝንብ (Black Soldier Fly) ተረፈ ምርት ለእንስሳት ምግብ የሚሆን በፕሮቲን የዳበረ ምግብና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረት መቻሉ ነው፡፡

ሚኒስቴሩ እንዳሳወቀው ኢትዮጵያ በያዘችው ዕቅድ መሠረት ከተሞች የማይበገር የምግብ ሥርዓት ፈጣሪ መሆን ይችላሉ፡፡ ሥርዓቱ ቴክኖሎጂን፣ ዘላቂነትንና ዑደታዊ ምጣኔ ሀብት (Circular Economy) መርሆዎችን ያካተተ ነው በማለት ይገልጹታል፡፡

በወደፊቱ ዓለም ከተሞች እየተስፋፉና የትኩስ ምግብ ፍላጎት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ፖሊሲ አውጪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ ግብርና በከተሜነትና በምግብ ዋስትና መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ መሸጋገሪያ ድልድይ ይሆናል ብለው ያምናሉ፡፡

ኢትዮጵያም ይፋ ያደረገችው አሰራር ከአሥር ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ የሚያደርጋት ይሆናል ተብሎ ይታመናል።

 

የከተማ ግብርናሰው ሰራሽ አስተውሎት

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!