እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:24:56 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

በቲክቶክ ላይ ያነጣጠረው የሳይበር ጥቃት መከላከያ መንገዶች

1 ደቂቃ ንባብ
በቲክቶክ ላይ ያነጣጠረው የሳይበር ጥቃት መከላከያ መንገዶች
 የሳይበር ወንጀለኞች የቲክቶክ ለንግድ (TikTok for Business) አካውንቶችን ለመዝረፍ የሚያስችል አዲስና ውስብስብ የማጭበርበሪያ (Phishing) ጥቃት ሰንዝረዋል።

በቅርቡ የወጡት የሳይበር ደህንነት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ በመረጃ ደህንነት ላይ ጉዳት ያደርሳል።  

ፑሽ ሴኪዩሪቲ (#Push_Security) የተባለው የደህንነት ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ጥቃቱ በተለይ የቲክቶክና የጎግል መልዕክቶችን በሚመስሉ የሐሰት ገጾች አማካይነት ይፈፀማል ።

ይህ አደገኛ የሳይበር ጥቃት በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች የሚከናወን ሲሆን፤ እነርሱም፦

#የማታለያ_ኢሜይል፦ መጀመሪያ "የሥራ ዕድል አለ" የሚል ማራኪ መልዕክት በኢሜይል አማካኝነት ለተጠቃሚዎች ይላካል።

#የሐሰት_ድረ_ገጽ፦ ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ፣ የቲክቶክ ወይም የጎግል መግቢያ ገጽን በትክክል የሚመስል ነገር ግን የሐሰት የሆነ ገጽ ይከፈትላቸዋል።

#የመረጃ_ስርቆት፦ ተጠቃሚው በዚያ ገጽ ላይ የተጠቃሚ ስምና የይለፍ ቃሉን (Password) ሲሞላ፣ መረጃው በቀጥታ በወንጀለኞቹ እጅ ይገባል።

ተጠቃሚዎች ከዚህ ጥቃት ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ ይመከራል፦

* አጠራጣሪ ሊንኮችን አይጫኑ፦ ከማያውቁት ሰው በኢሜይል የሚላኩ "የሥራ ዕድል" ወይም "ሽልማት" የሚሉ ሊንኮችን በፍጹም አይጫኑ።

* የድረ-ገጹን ስም ያረጋግጡ፦ ማንኛውንም መረጃ ከመሙላትዎ በፊት የሚገቡበት ድረ-ገጽ ትክክለኛው የተቋሙ አድራሻ (URL) መሆኑን በደንብ ያረጋግጡ።

* ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ፦ ማንኛውንም የይለፍ ቃል ከመሙላትዎ በፊት ገጹ ትክክለኛ መሆኑን ደግመው ያረጋግጡ ይላል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘው መረጃ።
የሳይበር ጥቃትኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂሳይንስና ቴክኖሎጂ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!