እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:26:32 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

በአማራ ክልል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተግባራዊ እየተደረገ ነው

1 ደቂቃ ንባብ
በአማራ ክልል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተግባራዊ እየተደረገ ነው
በአማራ ክልል የዲጂታል 2025 ምርጥ ተሞክሮን በማስፋት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በተሻለ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ነው::

በአማራ ክልል የዲጂታል 2025 ምርጥ ተሞክሮን በማስፋት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በተሻለ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ እስታወቀ።

በክልሉ 2025 ዲጂታል ኢትዮጵያ የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ በማስፋት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ቢሮው ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው ገልጸዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ተግባራዊ መደረጉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሰራራቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የህዝብ ቅሬታን መፍታት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ተሞክሮው በቀጣይ አምስት ዓመታት ለሚደረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሳለጥና ማደግ የጎላ አበርክቶ እንደሚኖረው በማመላከት።

በተጨማሪም ከአድሎ የፀዳ አሰራርን እውን በማድረግ የተጠቃሚውን እርካታ እንደሚያሳድገው ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል።

በክልሉ በርካታ ተቋማት አሰራራቸውን ዲጂታላይዝ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ ይህ የዲጂታላይዜሽን ትራንስፎርሜሽን ትግበራ የተሻለ ውጤት ታይቶበታል ብለዋል ለኢ,ዜአ

በተለይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ትግበራ የሕዝብ ቅሬታዎችን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዳስቻለ አቶ የቻለ አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተከናወነ  መሆኑን አብራርተዋል።

ዘመኑ ቴክኖሎጂን አብዝቶ መጠቀምን የሚጠይቅና ለዚህም ምህዳር መፍጠር የግድ በመሆኑ በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት እመርታዊ ለውጥ እየታየ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራን በሁለንተናዊ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋልና እንደ አገር የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!