እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:14:59 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የሚሳተፉ አትሌቶች ልምምድ ጀመሩ

1 ደቂቃ ንባብ
በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የሚሳተፉ አትሌቶች ልምምድ ጀመሩ
ውድድሩ የሚካሄድበት የአዲስ አበባ ስታዲዬም ከስምንት ዓመታት በኋላ የመሮጫ መም እድሳቱ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
1 / 2
የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶች ዛሬ ልምምድ ማድረግ ጀመሩ።

የዓለም አትሌቲክስ የሚያስተዳድረው ተቋም ዓመታዊ አህጉራዊ ውድድር አካል የሆነው የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን ውድድር በኢትዮጵያ የሚካሄደው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ውድድሩ የሚካሄድበት የአዲስ አበባ ስታዲዬም ከስምንት ዓመታት በኋላ የመሮጫ መም እድሳቱ ተጠናቅቆ ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ውድድሩ ዓለም አትሌቲክስ የነሐስ ደረጃ  የተሰጠው ሲሆን፥ተወዳዳሪዎችም ወደ ከተማዋ በመግባት ላይ ናቸው ፡፡በውድድሩ የሚሳተፉ አትሌቶችም ልምምድ ሲያደርግ ውለዋል፡፡

የስታዲዬሙ መሮጫ ትራክ በዓለም አቀፍ ውድድር ለሚሳተፉ አትሌቶች ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በዚህም የመሮጫው ትራክ በአዲስ መልክ እድሳት ተደርጎለት አሁን ለውድድርና ለልምምድ ዝግጁ መሆኑን ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የአንድ ቀን ውድድር ስኬታማ እንዲሆን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የመሮጫ መም እድሳቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ላደረገው ርብርብ ምስጋናውንም አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገትና ልማት የሰጠው ልዩ ትኩረት ለስፖርቱ መነቃቃት የማይተካ ሚና እንዳለው ፌዴሬሽኑ አመላክቷል።




  
ስፖርትየአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪአትሌቲክስ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!