እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:26:26 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሕግና ፍትሕ

በአዲስ አበባ 40 ኪሎ ግራም ካናቢስ በቁጥጥር ሥር ዋለ

2 ደቂቃ ንባብ
 በአዲስ አበባ 40 ኪሎ ግራም ካናቢስ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ከባንኮክ ተነስቶ ጆሃንስበርግ መዳረሻው የሆነ አውሮፕላን ትራንዚት ሲያደርግ በረቀቀ መልኩ በሻንጣ ውስጥ የተደበቀ 37 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ተይዟል።
1 / 2

በአዲስ አበበ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊተላለፍ የነበረ 40 ኪሎ ግራም ካናቢስ አደንዛዥ ዕጽ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እንደገለጸው፤የተለያዩ አቅጣጫዎች መነሻና መድረሻው አድርገው አዲስ አበባን መተላለፊያ ባደረጉት በረራዎች በተደረገው ቁጥጥር ኮኬይኑ ሊያዝ ችሏል።

የመጀመሪያው ከታይላንድ ባንኮክ ተነስቶ  ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ መዳረሻው የሆነ አውሮፕላን በአዲስ አበባ  በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ትራንዚት ሲያደርግ በረቀቀ መልኩ በሻንጣ ውስጥ የተደበቀ 37 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ አደንዛዥ ዕጽ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ 

የእንግሊዝ ዜግነት ያለው  የአደንዛዥ ዕጹ አዘዋዋሪም ተይዞ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይም ከፈረንሳይ ፓሪስ ወደ ኮሞሮስ ዋና ከተማ ሞሮኒ ሲጓዝ በነበረ አውሮፕላን ላይ በሻንጣ የውስጥ አካል ላይ በረቀቀ መልኩ የተደበቀ 3 ነጥብ 160 ኪሎ ግራም የሚመዝን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በትራንዚት በኩል ለማሳለፍ ሲሞከር ተይዟል፡፡

አደንዛዥ ዕጾቹ በተዘረጋው ግልጽ የአሰራር ሠርዓት አማካኝነት ከባለድርሻ አካላት ጋራ በመቀናጀትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በተከናወኑ ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር መያዛቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡

ዑጋንዳዊቷ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ውስጥ በረቀቀ መልኩ 500 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ደብቃ ለማስተላለፍ ስትሞክር ትናንት በቁጥጥር ሥር ውላለች፡፡

በያዝነው ሣምንት መጀመሪያም ከአራት ኪሎ ግራም በላይ ኮኬይን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አገልግሎቱ አስታውሷል።

ኢትዮጵያ የበርካታ አፍሪካ አገሮች መተላለፊያ ከመሆኗም ባሻገር፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ተመራጭ የትራንዚት ማዕከልነቷ በመጠናከሩ ከሰላማዊ ተጓዦች ጋር ተቀላቅለው በሕገ-ወጥ ተግባራት የሚሰማሩ በመኖራቸው እንደ ወትሮው ሁሉ በከፍተኛ ዝግጁነት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ያደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የላቁ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም መቻሉ፤ የሰው ኃይል አቅም መገንባቱ እንዲሁም ግልጽ አሠራር መዘርጋቱ በአውሮፕላን ማረፊያው የሚተላለፉ አደንዛዥ ዕጾችና ሌሎችንም ሕገ-ወጥ ቁሶች በከፍተኛ ደረጃ መቆጣጠሩን አመልክቷል።

በተከታተይ ቀናት በአውሮፕላን ማረፊያው አደንዛዥ ዕጽ ለማስተላለፍ ሲደረጉ የነበሩ ሙከራዎች እንደወትሮው ሁሉ በሚከናወኑ ጥብቅ ፍተሻና የቁጥጥር ሥርዓቶች አለመሳካታቸውን ያስታወሰው አገልግሎቱ፤  የአገርን ብሔራዊ ደኅንነትና የኢትዮጵያ አየር መንገድን መልካም ስምና ገጽታ የሚጎዱ መሰል ወንጀሎችን በከፍተኛ ዝግጁነትና በተደራጃ መንገድ ለመከላከል እርምጃዎቹ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብሏል አገልግሎቱ፡፡

አደገኛ ዕጽወንጀል

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!