እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:51:50 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

በወርቅ ሜዳሊያ የተመረቁት የጤና ዘርፍ ከዋክብት

1 ደቂቃ ንባብ
በወርቅ ሜዳሊያ የተመረቁት የጤና ዘርፍ ከዋክብት
ለዚህ ውጤት ያበቃኝ የእኔ ትጋት ብቻ ሳይሆን፣ የቤተሰቦቼ ድጋፍና ክትትል ጭምር ነው" የምትለው ፍቅር፤ "ሰው ለዓላማው መሳካት ፈተናዎችን መቋቋም አለበት"ስትልም አክላለች።
1 / 2

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዛሬ ካስመረቃቸው 255 የሕክምና ባለሙያዎች መካከል፣ ሁለት ስሞች በልዩ ክብር መድረክ ላይ በጉልህ ተደምጠዋል።

እነዚህ ወጣቶች በትጋትና በዓላማ መመሳሰል ብቻ ሳይሆን፣ ሁለቱም 3ነጥብ 98 ድንቅ ውጤት በማስመዝገብ የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን በወርቅ ሜዳሊያ አጠናቀዋል።

በፊዚዮቴራፒ የትምህርት ዘርፍ ኮከብ ሆና የወጣችው ፍቅር ገብሩ፣ ለስኬቷ ምስጢር ከግል ጥረቷ ባሻገር የቤተሰቦቿን ያልተቋረጠ ድጋፍ ትጠቅሳለች። 

"ለዚህ ውጤት ያበቃኝ የእኔ ትጋት ብቻ ሳይሆን፣ የቤተሰቦቼ ድጋፍና ክትትል ጭምር ነው" የምትለው ፍቅር፤ "ሰው ለዓላማው መሳካት ፈተናዎችን መቋቋም አለበት" የሚል ፅኑ እምነት አላት። 

ፍቅር አሁን የያዘችውን ዕውቀት ተጠቅማ ነገ የተጎዱ ሰዎችን ለማከምና ለማህበረሰቧ "የፈውስ እጅ" ለመሆን በጉጉት ትጠባበቃለች።

በሌላኛው የጤና ዘርፍ በነርሲንግ ደግሞ ነብዩ ዳዊት የልህቀት ማማውን ተቆጣጥሮታል። 

የነብዩ ስኬት የዛሬ ጅማሮ ሳይሆን፤ገና ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ የነበረ የትጋት ውጤት ነው። 

ለነብዩ ነርሲንግ ማለት የጤና ዕውቀት ብቻ ሳይሆን፣ ሰብዓዊነትና ሥነ-ምግባር የታከለበት ታላቅ አገልግሎት ነው ይላል የኢቢሲ ዘገባ። 

"ማህበረሰቤን በቅንነት ማገልገል እፈልጋለሁ" የሚለው ነብዩ፣ አገራችን ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት በሙያው ለመደገፍ ቃል ገብቷል።

ፍቅርና ነብዩ የውጤት ባለቤቶች ብቻ አይደሉም፤ ለብዙ ተማሪዎች አርአያ፣ ለወላጆቻቸው ኩራት፣ ለአገራቸው ደግሞ አዲስ የጤና አርበኞች ናቸው። 





ትምህርትከፍተኛ ትምህርትምረቃ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!