
አትሌት ብርቅነሽ ደሴ የ23ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አሸንፋለች።
ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ለ23ኛ ጊዜ "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ተደርጓል።
በውድድሩ ላይ 16 ሺህ ሴቶች፣ ከ150 በላይ አትሌቶችና 25 ተምሳሌት ተብለው የተሰየሙ ሴቶች ተሳትፈዋል።
በአትሌቶች መካከል በተደረገው ውድድር ብርቅነሽ ውድድሩን ያሸነፈችው ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ ነው፡፡
የጸደይ ባንክ ስፖርት ክለብን ወክላ የምትወዳደረው ብርቅነሽ አምና ውድድሩን አጠናቃለች፡፡
መነሻውን መድረሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል በማድረግ በተካሄደው ውድድር ሮቤ ዲዳ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡
ብርቅነሽና ሮቤን ተከትላ ሦስተኛ የወጣችወ ሰናይት ጌታቸው ናት።
ውድድሩን ከ35 ደቂቃ በላይ ተሳታፊዎች በአትሌት መሠረት ደፋር የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ውድድርም ተካሂዷል፡፡
በሁነቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስጀመሩት ሲሆን፣የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሠረት ደፋር፣ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ውድድሩ የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ከ1996 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!