እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:50:25 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ

1 ደቂቃ ንባብ
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ  ጀመረ
ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳውን በመላው ኢትዮጵያ ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ የፓርቲውን ፖሊሲዎችና አማራጮች ለዜጎች የሚያስረዳ ሲሆን፣ የቅስቀሳ ሥራውን ሲያከናውን ሕዝቡ ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግለት ጠይቋል።
በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደረው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ የምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩን አስታውቋል።

የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ  ፓርቲያቸው በመላ ኢትዮጵያ በሚካሄደው ምርጫ ላይ በቁርጠኝነት ለመሳተፍ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የቅስቀሳ ሥራውን መጀመሩን ገልጸዋል።

ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲጎለብትና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ቁልፍ ሚና እንዳለው ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

ሕዝቡም በቀሩት ቀናት ውስጥ የመራጭነት ካርድ እንዲያወጣ፣ በምርጫው ሂደት በንቃት በመሳተፍ ለዴሞክራሲ መጎልበት ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርበዋል።

ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳውን በመላው ኢትዮጵያ ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ የፓርቲውን ፖሊሲዎችና አማራጮች ለዜጎች የሚያስረዳ ሲሆን፣ የቅስቀሳ ሥራውን ሲያከናውን ሕዝቡ  ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግለት ጠይቋል።

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ (አግን)፣ እናት ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅንጅት የፈጠሩት ፓርቲ ነው።

ለሰባተኛው ጠቅላላ  ምርጫ የመራጮች ምዝገባ አሰየተካሄደ ሲሆን፤እስከ መጋቢት 24ቀን 2018 ድረስ ከ36 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል።


ምርጫትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲየፖለቲካ ፓርቲዎችምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!