እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:28:15 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሕግና ፍትሕ

ኅብረተሰቡ ኦ ኬ(OK) በረኪናን እንዳይጠቀም ተመከረ

1 ደቂቃ ንባብ
ኅብረተሰቡ ኦ ኬ(OK) በረኪናን እንዳይጠቀም ተመከረ
ሚኒስቴሩ የበረኪናውን ወካይ ናሙና በመውሰድ በተደረገው የላቦራቶሪ የጥራት ፍተሻ ውጤት መሠረት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃና የጥራት መስፈርት ያላሟላ በመሆኑ የኀብረተሰቡን ጤናና ደህንነት እንዲሁም ጥቅም ከማስከበር አንጻር ምርቱ ጥቅም እንዳይውል ታግዷል።

ኅብረተሰቡ ኦኬ(OK)የተባለውን የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የማያሟላና የጥራት ችግር በረኪና አንዳይጠቀም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን  የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃ መስፈርት ማሟላታቸውን ይቆጣጠራል።

ከደረጃ በታች ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ በመውሰድ የኅብረተሰቡን ጤንነት፣ ደህንነትና ጥቅም ያስጠብቃል፤ለዚህም የደረጃም ሆነ የየጥራት ቁጥጥርና ክትትል ሥራዎችን እንደሚያከናውን አብራርቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ዛሬ እንዳስታወቀው በምርቱ ላይ ላይ በተደረገው የእይታ ፍተሻ መሠረት በምርቱ ላይ የአምራች ስም፣አድራሻና ብሔራዊ የደረጃ ምልክት የለውም።

በምርቱ በተደረገው የላቦራቶሪ የጥራት ፍተሻ ውጤትም አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን የማያሟላና የጥራት ችግር እንዳለበት ተረጋግጧል ብሏል።

ሚኒስቴሩ በገበያ ላይ ባደረገው ኢንስፔክሽን የበረኪናውን ወካይ ናሙና በመውሰድ በተደረገው የላቦራቶሪ የጥራት ፍተሻ ውጤት መሠረት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ CES 234:2023 የደነገገውን የጥራት መስፈርት ያላሟላ መሆኑን ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

የኀብረተሰቡን ጤናና ደህንነት እንዲሁም ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ይህን ምንጩ የማይታወቅና የጥራት ችግር ያለበትን ምርት ጥቅም እንዳይውል አግዷል።

በየደረጃው በሚገኙ የክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮዎች በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግና ማንኛውም ነጋዴ በገበያ ቦታ፣ በንግድ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ ይህን ምርት ሲሸጥ ከተገኘ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል፡፡

ኀብረተሰቡ ምርቱን እንዳይጠቀም ሚኒስቴሩ አጥብቆ አስስቧል፡፡

የጥራት ደረጃዎችአስገዳጅ ደረጃዎችንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማኒስቴር

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!