
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አትላንታ ዳግም በረራ ሊጀምር ነው።
አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣወ መግለጫ እንዳስታወቀው አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ ተቋርጦ የነበረውን በረራ በግንቦት ወር ይጀምራል።
በረራው ባለፈው ወር የተቋረጠውን አገልግሎት ዳግም ለማስቀጠል እንደሚያስችለውም አመልክቷል።
በረራው በአፍሪካና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመመለስ ያስችላል ብሏል መግለጫው።
በአዲስ አበባና በአትላንታ መካከል የሚካሄዱት በረራዎች አትላንታን ከኢትዮጵያ አየር መንገዶች በረራ መሥመሮች ጋር በማገናኘት የላቀ ድርሻ እንደሚጫወትም ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሥፍን ጣሰው በሰጡት አስተያየት"አትላንታ አየር መነገዲ በአሜሪካ ካሉት የበረራ መሥመሮች ከፍተኛ ገቢ ከምናገኝባቸው መካከል ናት።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ የበረራ መሥመር አገልግሎት መስጠት የሚጀምር በመሆኑ ደስተኛ ነው።መሥመሩ እያደገ የመጣውን የንግዱን ማህበረሰብ፣የአፍሪካ ዳያስፖራና ቱሪስቶችን በተመቻቸ ሁኔታ የአፍሪካ መዳረሻዎች ለመገልገል ያስችላቸዋል"ብለዋል።
አትላንታ በአሜሪካ ዋነኛዋ የኢኮኖሚና የባህል ማዕከል ስትሆን፣በአገሪቱ ካሉት የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በከተማዋ ይኖራሉ።
አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ ዳግም የሚያስጀምረው በረራ ከአገሪቱ ደቡብ ምሥራቅ የሚገኙ ከተሞች የሚመጡ መነገደኞችን በአዲስ አበባ በኩል ከአፍሪካ ለማገናኘት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው መግለጫው አስረድቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ በረራ የሚያደርግባቸው በርካታ መሥመሮች ያሉት ሲሆን፣ከአትላንቲክ ባሻገር ያሉትን መሥመሮቹን ለማጠናከር የረጅም ጊዜ የዕድገት ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ወደ አትላንታ የሚደረገው በረራ ዳግም መጀመር መንገዱ አፍሪካን ከሌላው ዓለም የሚያገናኝ ድልድይ ሆኖ ለማገልገል እንደሚያስችለውም ታምኖበታል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!