
አንጋፋዋ ዲፕሎማት "የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ኢንሳይክሎፒዲያ" ተብለው ይታወቁ ነበር።
ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት(አአድ)ወቅት ካገለገሉ ቀደምት ዲፕሎማቶች መካከል የሚጠቀሱ፤ድርጅቱ ወደ አፍሪካ ኅብረት ሲሸጋገርም ሙያዊ አስተዋጽ አበርክተዋል።
አምባሳደር ቆንጂት በ19555 ሥራ ሲጀምሩ በኢትዮጽያ የዲፕሎማሲው መስክ ለሴቶች እምብዛም ክፍት አልነበረም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዕረፍታቸውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ይህንንና ለአገራቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ አመላካች ነው።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን ያለፈ አገልግሎት ያላቸው ዲፕሎማት በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተመድበው በፀረ ቅኝ አገዛዝ ጉዳዮች የሚከታተል ክፍል ውስጥ ሲያገለግሉ ለአፍሪካ ነፃነት ግንባር ቀደም ሆነው መታየት የጀመሩባቸውን ተግባራት በማከናወን ዕውቅና ማግኘት የጀመሩበት ወቅት ነበር።
ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካውያን መብቶችና ጥቅሞች መከበር የታገሉት አምባሳደር ቆንጂት በ86ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት ዛሬ ነው።
አገራቸውን በኦስትሪያ፣በግብፅ፣በአሥራኤል፣በካናዳና በሜክሲኮ በአምባሳደርነት ማገልገላቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።"ሥራዬ ሕይወቴ ነው፤ለእሱም ሕይወቴን ሰጥቼያለሁ"በሚል መርህም ሕይወታቸውን እንደሚመሩም በአንድ ወቅት ተናግረዋል።ይህንንም የሙያ ባልደረቦቻቸው ይመሰክሩላቸዋል።
ኢትዮጵያን በተከታታይ መንግሥታት በማገልገል ክብርና ምስጋና የተቸራቸው አንጋፋ ዲፕሎማት ሆነውም አገልግለዋል።
አምባሳደር ቆንጂት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዕወቅና የሰጡበትን ሽልማት ተቀብለዋል።
እንዲሁም በ2008የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል።
አምባሳደር ቅንጂት ከጃፓን መንግሥትና ከታላላቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሽልማቶች መቀበላቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!