
ኢትዮጵያና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር አስታወቁ።
የዓለም ባንክና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ስብስባ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው ።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከስብሰባው በተጓዳኝ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤን ብላክ ጋር ተመካክረዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያና ኮርፖሬሽኑ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ላይ ያተኮረ የነበረ ሲሆን፣በተለይም በትራንስፖርትና ማዕድን ዘርፎች ትብብር ላይ የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን የገንዘብ ሚስቴር ያሰራጨው መግለጫ ያመለክታል።
ተወያዮቹ ዘላቂና አካታች እድገትን ለማፋጠን የልማት ፋይናንስ ያለውን ወሳኝ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይም መክረዋል።
ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የኢንቨስትመንት ኢኒሼቲቮች ለማሳለጥ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት በማስመልከት አቶ አህመድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
መንግሥት ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ።
ኮርፖሬሸኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተለይም በመሠረተ ልማትና በሌሎች ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በኢትዮጵያ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለውን ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።
ሁለቱም ወገኖች የፋይናንስ ዕድሎችን ለመጠቀምና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ውጤቶችን ለማምጣት ትብብር አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተው መነጋገራቸውን መግለጫው አመላክቷል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!