እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:50:52 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፓሪስና በብራዚሊያ

1 ደቂቃ ንባብ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፓሪስና በብራዚሊያ
1 / 2
በሣምንቱ መጨረሻ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

ከነዚህም ዛሬ የፓሪስ ማራቶን ውድድር አትሌት ሹሬ ደምሴ አሸንፋለች።

ሹሬ ርቀቱን 2 ሰዓት 18 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌት ምስጋኔ አለማየሁ ርቀቱን 2 ሰዓት 19 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት በውድድሩ ሁለተኛ ሆናለች።

አትሌት እናትነሽ አላምረው ደግሞ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ፈጽማለች።

በወንዶች ምድብ ጣሊያናዊው አትሌት የማነብርሃን ክሪፓ 2 ሰዓት 05 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል።

የማነብርሃንን በመከተል አትሌት ባየልኝ ተሻገር 2 ሰዓት 05 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ በመሆን ፈጽሟል።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ርምጃ ውድድር የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ በአትሌት ምስጋና ዋቁማ አግኝታለች።

በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚሊያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የእርምጃ የቡድን ሻምፒዮና ላይ በወንዶች የእርምጃ ግማሽ ማራቶን የተወዳደረው ምስጋና ዋቁማ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

ውጤቱ በኢትዮጵያ የእርምጃ ውድድሮች ተሳትፎ ታሪክ የመጀመሪያውን የዓለም አቀፍ ውድድር የተገኘ ድል  መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

አትሌት ምስጋና ውድድርሩን ያጠናቀቀው በአንድ ሰዓት ከ27:33 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓት ነው፡፡

በሴቶች የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር  አትሌት ህይወት አምባው ዘጠነኛ፤በዚሁ ርቀት የተወዳደረው አብዱሰላም አብዱልወሀብ  11ኛ ወጥቷል፡፡



 

ስፖርትአትሌቲክስ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!