
የአፍሪካ ዋንጫ የ2027 ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔን የገጠመችው ኢትዮጵያ በድምር ውጤት አራት ለባዶ በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅላለች።
በሞሮኮ የተደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ያሸነፉት ዋልያዎቹ በድሬዳዋ ስታዲየም የተከናወነውን የመልስ ጨዋታ አንድ ለባዶ መርታት ችላለች።
ከአምስት ዓመታት በኋላ በአገሩ ለተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቸርነት ጉግሳ ብቸኛውን ግብ በሰባተኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
ዋልያዎቹ በቀጣይ በኬንያ ፣ ታንዛንያና ዩጋንዳ አዘጋጅነት ለሚደረገው የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ የሚያደርጉ ይሆናል።
በጨዋታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይበልጥ ጨዋታ መቆጣጠር ላይ በማተኮሩ ተጨማሪ ግቦች ለማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።
ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውነ በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፉና ረጅም ጉዞ አድርጎ ወደ ሜዳ በመግባቱ ጨዋታውን ቁጥጥር ላይ እንዲጠመድ ያደረገው መሰሏል።
ከረጅም ጊዜ በኋላ በአገሩ ምድር የተጫወተውን ብሔራዊ ቡድናቸው በርካታ ደጋፊዎች በድሬዳዋ ስታዲዬም በመገኘት አበረታተውታል።
የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ማጣሪያዎች በ2019 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ይደረጋሉ።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!