
ተቋሙ ደረጃውን የሚለከባቸው መመዘኛዎች የብሐራዊ ቡድኑ ጥንካሬ፣ የሚያከናውናቸው ጨዋታዎች ያላቸው ወሳኝነት፣ በጨዋታዎቹ የሚያገኘው ውጤትና ከጨዋታዎቹ በፊት የሚጠበቁት ውጤቶች ናቸው።
የተቋሙ የተጠናቀቀው ማርች 2025 ሪፖርት አንደደሚያሳየው ኢትዮጵያ 144ኛ ደረጃ ይዛለች።ይህም ከነበረችበት 147ኛ ደረጃ ሦስት ደረጃዎች ማሻሻሏን ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔን አራት ለባዶ በማሸነፍ ወደ ምድብ ማጣሪያው ማለፉ ደረጃውን ለማሻሻል አስችሎታል።
ከአፍሪካ አህጉር ሞሮኮ ከአፍሪካ አንደኛ፣ ከዓለም ደግሞ ስምንተኛ ደረጃ ይዛለች።
በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆኑትን ደረጃዎች ከያዙት መካከል ሴኔጋል 14ኛ፣ ናይጄሪያ 26ኛ፣ አልጄሪያ 28ኛ፣ ግብጽ 29ኛ ናቸው።
እንዲሁም ኮትዲቯር 34ኛ፣ ቱኒዚያ 44ኛና ካሜሩን 45ኛ ደረጃ ይዘዋል።
ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ደረጃዋን ከ48ኛ ወደ 46ኛ አሻሽላለች።
አገሪቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ለቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ያለፈች አገር መሆኗም ይታወቃል።
በዓለም ጀረጃ በተቀመጠው ደረጃ ፈረንሳይ የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፣ስፔን ሁለተኛ ሆናለች።
የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ አርጀንቲና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ከአራተኛ እስከ ሰባተኛ ያሉትንጨደረጃዎች የተቆጣጠሩት እንግሊዝ፣ ፖርቹጋል፣ ብራዚልና ኔዘርላንድስ ናቸው።
ጣልያን 12ኛ ደረጃን ይዛለች።
ሳን ማሪኖ በዓለም እግር ኳስ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛ 211ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሪፖርቱ ያሳያል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!