
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ በክልሉ አቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ያስፈለፈላቸውን ከ6 ሺህ በላይ የአንድ ቀን ዶሮ ጫጩቶችን ለአርቢዎች አሰራጨ፡፡
በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው የዶሮ እርባታ ሥራ ልምድ የሚወሰድበት ነው ብለዋል፡፡
ማዕከሉ መልኩ ከተደራጀ በኋላ ባጋጠመው የአቅርቦት እጥረት ምክንያት በሚፈለገው ፍጥነትና መጠን አገልግሎት ለመስጠት ሲቸገር መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
የክልሉን ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ አቅም ለማጎልበት ግዙፍ አቅም ያለው የእንቁላል ማስፈልፈያ ማሽን ግዥ እያካሄደ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።
በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ6ሺህ በላይ የአንድ ቀን ዶሮ ጫጬቶችን በማስፈልፈል ለዶሮ አርቢዎች ለማሠራጨት በመብቃቱም አድንቀዋል።
የክልሉ የዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ አዲሱ ኢዮብ(ዶ/ር) በበኩላቸው የዶሮ ሀብት ልማት ሥራ ጊዜ፣ ጉልበትና ትኩረት ይሻል ብለዋል፡፡
ሥራው በትንሽ ቦታ ብዙ ትርፍ የሚሰጥ፣ የምግብና ሥነ-ምግብ ሥርዓትን የሚያሻሽል፣ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያስጠበወቅ በመሆኑ ማህበረሰቡ በስፋት ሊሳተፍበት ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያስረዳል፡፡
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!