እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:28:32 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ኤ ኤም ኤን የምርጫ 2018 ክርክሮችን ማስተናገድ ጀመረ

1 ደቂቃ ንባብ
ኤ ኤም ኤን የምርጫ 2018 ክርክሮችን ማስተናገድ ጀመረ
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የምርጫ 2018 ክርከሮችን በማስተናገድ ሦሰተኛው መገናኛ ብዙኃን ሆኗል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚተዳደረው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ(ኤ ኤም ኤን) በምርጫ 2018 የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማከራከር ጀመረ፡፡

ጣቢያው ክርክሮቹን በማስተናገድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(ኢቢሲ)ና ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን(ፋና) ቀጥሎ ሦስተኛው መገናኛ ብዙኃን ሆኗል፡፡

ጣቢያው በአምስት ዙሮች  ከሚያዘጋጃቸው ክርከሮች የመጀመሪያውን ‹‹የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ››በሚል ርዕስ አስተናግዷል፡፡

በክርከሩ ኀብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፣ብልጽግናና ህዳሴ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውንና አቋሞቻቸውን ያንጸባሩበትን ክርከር ያደረጉበትን ክርክር አድርገዋል፡፡

 ጣቢያው በአምስት   ዙሮች በሚያካሂዳቸው ክርክሮች 21 አገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ክርክሮች  በተመረጡ ርዕሶች እንደሚያካሂድ ተመላክቷል፡፡

ጣቢያው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤትና ከፓርቲዎቹ ጋር የካቲት 21 ቀን 2018 ባደረገው ውይይት አምስት የመከራከሪያ ርዕሶች ባወጡት ዕጣ መሠረት ይከራከራሉ፡፡

ፓርቲዎቹ ቢመረጡ በአገርና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚተገብሯቸውን ፖሊሲዎችና ያሏቸውን አማራጮች ለመራጩ ሕዝብ በጣቢያው እንደሚያቀርቡም ተገልጧል፡፡

ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ግን በሁሉም ክርክሮች እንዲሳተፍ መወሰኑን ከጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

 

መገናኛ ብዙኃንክርከርምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!