እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:16:03 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ከአዲስ አበባ እስከ ፕሪቶሪያ

3 ደቂቃ ንባብ
ከአዲስ አበባ እስከ ፕሪቶሪያ
አሜሪካዊቷ የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ጋቢ ቶማስ በውድድሩ ከሚካፈሉ ከዋክብት መካከል ናት::

ከአዲስ አበባ እስከ ፕሪቶሪያ ያለው መንገድ የዓለም ሻምፒዮናዎቹ ሰሞኑን በሚያካሂዷቸው ውድድሮች ይደምቃሉ፡፡ሻምፒዮኖቹ ከዓለም ዳርቻዎች ተጠራርተው ወደ አፍሪካ ያመራሉ፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ውድድሮች የበርካታ ወርቅ  ሜዳሊያ ባለቤቶች በሚቀጥሉት ሁለት ሣምንታት መገኛቸ አፍሪካ ይሆናል፡፡በአህጉራዊ ውድድሮች ሳቢያ ማረፊያቸው አሀጉሪቱ ትሆናለች፡፡የመጨረሻ መዳረሻቸው በቦትስዋና  ርዕሰ ከተማ የጋቦሮኒ ዴብስዋና አተሌቲክስ ሪሌይ ይሆናል፡፡

መነሻቸው ከተባለ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲናው አዲስ አበባ ናት፡፡

የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮችን የሚመራው የዓለም አትሌቲከስ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ አገሮችን የሚያዳርሱ አሀጉራዊ ውድድሮችን አሰናድቷል፡፡በአፍሪካ አሀጉር ያዘጋጀው ውድድር ደግሞ መነሻውን አዲስ አበባ  ሚያዝያ 10 ቀን 2018 በሚደረግ ውድድር ይጀመራል፡፡

ቀጣዩን ውድድር የወርቅ ደረጃ ያለው በኬንያ ናይሮቢ የሚደረገው ውደድር ሚያዝያ 17 ይደረጋል፡፡ቀጥሎ የወርቅ ደረጃ ያለው ውድድር ሚያዝያ 19 የምታስናግደው ጋቦሮኒ፤ቦትስዋና ትሆናለች፡፡

ከሦስቱ ውድድሮቸ በኋላ ውድደሮችን ለማስተናገድ ዕድል የምታገኘው የደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ ከተማ ሲምቢኒ ክላሲክ የተሰኘ ውድድር ሚያዝያ 21 ይካሂድባታል፡፡ከዚ,ያም ወደ ቦትስዋና ተመልሶ ሚያዝያ 24 25 ቀናት የጋቦሮኒ ሪሌይ ውድድሮች ይስተናገዱባታል፡፡

በነዚህ ውድድሮች ለሚካፈሉት ተወዳዳሪዎች መካከል አሜሪካዊቷ የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ጋቢ ቶማስ በውድድሩ ከሚካፈሉ ከዋክብት መካከል ናት፡፡የ29 ዓመቷ አትሌት በፓሪስ ኦሎምፒክ በ200 ሜትር፣በ4*400 ሜትርና በ4*400 ሜትር ውድድሮች ወርቅ ያገኘች ናት፡፡

በአዲስ አበባው ግራንድ ፕሪ ውደድር የፊታችን ቅዳሜ  ከአገሯ ልጅ ዳሊያህ ሙሐመድ ጋር ትዳደራለች፡፡ዳሊያህ በ2016 ኦሎምፒክና በ2019 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ400 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈች አትሌት ናት፡፡

ከሁለቱ በተጨማሪ የ2022 የዓለም የቤት ውስጥ የ60 ሜትር መሰናክል ውድድር አሸናፊዋ ፈረንሳዊቷ ሲይሪና ሳምባ ማይላ ሌላዋ የአዲስ አበባው ግራንድ ፕሪ ተወዳዳሪ ትሆናለች፡፡

የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የየነሐስ ደረጃ ውድድርን ሚያዝያ 10 ቀን 2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም በማካሄድ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውደድሮችን የምታሰተናግድበትን አቅምና ልምድ ለማሳደግ እንደሚረዳት ታምኖበታል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድሩ የሚካፈሉ አትሌቶችንና የሚሳተፉባቸውን የውድድር ዓይነቶች መረጃ በመስጠት ላይ ሲሆን፣ተመልካቾችም ውድድሮቹን በአካል ተገኝተው እንዲከታተሉ በመጋበዝ ላይ ነው፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውድድሩን በብቃት ለማስተናገድ ሁለንተናዊ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን በሰጠውመግለጫ አስታውቋል፡፡

አገሪቱ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ከማሰናዳት ያላለፋትን ልምድ ወደተሻለና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ወደምታስተናግድበት ደረጃና አቅም ያስችላታል ተብሎም ይታሰባል፡፡

በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብፅ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሌሶቶ፣ ኦማንና ሳዑዲ ዓረቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሳሳይ ውድድሮችን ያዘጋጃሉ።

በመዶሻ ውርወራ ድንቅ ውጤት ያላት ካናዳዊቷ ካምሪን ሮጀርስ በኬንያው ውድድር የምትሳተፍ የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮና አትሌት ነች፡፡አትሌቷ የዓመቱን ውድድር በአሜሪካ ኦስቲን ከተማ 81ሜትር ከ13 ሳንቲ ሜትር በመወርወር ነው የጀመረቸው፡፡

አሜሪካያውኑ እንስት የአዲስ አበባዎቹ ድምቀቶች በቦትስዋናው ግራንድ ፕሪ ይወዳደራሉ፡፡ካናዳዊው ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት አንድሬ ዴ ግራስና የደቡብ አፍሪካው ተወላጅ የዓለም 400 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት ዋይዴ ቫን ኒከሬክ እንዲሁም 100 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት ፈርዲናንድ ኦማንያላ ሌሎቹ ተሳታፊዎቹ መሆናቸውን የተቋሙ መረጃ ያሳያል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በምታስተናግደው የፕሪቶሪያ ሲምቢኒ ክላሲክ የ100 ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት አካኒ ሲምቢኒ ይወዳደራል፡፡በ300 ሜትር ዛምቢያዊው የ400 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሙኮላ ሳሙኮንጋ፣ከሌሎቹ ደቡብ አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎች ዙኪቲ ኔኔና ልይዝ ፒሌይ በዚሀ  ውድድር ይገናኛሉ፡፡

አህጉራዊ ውድድሮች በአራት ዐበይት ምድቦች ይካሄዳሉ፡፡ምድቦቹ ወርቅ፣ብር፣ነሐስና ቻሌንጀር የሚል ስያሜ አላቸው፡፡ተውድድሮቹ ደረጃ የሚወሰነው ባላቸው የጥራት ደረጃና በሚያስገኙት የገንዘብ ሸልማት መጠን ነው፡፡

በነዚህ ውድድሮች ቢያንስ 30 አገሮች ተወዳዳሪዎች የሚካፈሉባቸው በወርቅ፣በብርና በነሐስ ደረጃዎቸ የተዘጋጁት የናይሮቢ፣የጋቦሮኒ፣የፕሪቶሪና የአዲስ አበባ ውድድሮች ይካሄዱባቸዋል፡፡

የተቋሙ ውድድሮችና ሁነቶች መምሪያ አህጉራዊ ውድድሮች ያላቸወን ፋይዳ በመገንዘብ እንዲዘጋጁ ማድረጉንና በዚህም አፍሪካ ውድድሮችን ለማዘጋጀትና የአትሌቲክስ ማሀበረሰብ በሚያደርገው ተሳትፎ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አትሌቶቹ በውድድሮቹ በሚያስመዝገቡባቸወ ውጤቶች የሚያጠራቅሟቸው ነጥቦች  ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች የሚያስጠጋቸው ደረጃ ለመያዝ ይረዳቸዋል ብሏል፡፡

ተቋሙ እስከ ኀዳር  2019 በሚያካሂዳቸው ውድድሮች በመላው ዓለም 290 ውድድሮች እንደሚካሄዱም መረጃው አመላክቷል፡፡
ስፖርትአትሌቲክስየአንድ ቀን ግራንድ ፕሪ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!