እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:24:46 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ከአገሪቱ ንግድ ባንኮች በአስተማማኝ መሠረት የሚገኙት አምስቱ ብቻ ናቸው

1 ደቂቃ ንባብ
ከአገሪቱ ንግድ ባንኮች በአስተማማኝ መሠረት የሚገኙት አምስቱ ብቻ ናቸው
በአገሪቱ ያሉት 25ቱ የንግድ ባንኮች ተዋህደው ጠንካራ ባንኮችን መፍጠር ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡

በአገሪቱ ካሉት 31 የንግድ ባንኮች በአስተማማኝና ጥሩ መሠረት  ላይ የሚገኙት አምስቱ ብቻ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

በአገሪቱ ያሉት 25 የንግድ ባንኮች ተዋህደው ጠንካራ ባንኮችን መፍጠር ብቸኛው አማራጭ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

ባንኩ ዘርፉን በገመገመበት ሰነድ አንዳመለከተው፤በኢትዮጵያ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት ባንኮች በሦስት ደረጃዎች ትልቅ ፣መካከለኛና ትንሽ በሚል  ምድቦች ባንኮች ከፍሏቸዋል፡፡

በዚህም  ትልቅ የተባለው  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን፣ በአገሪቱ ባንክ ዘርፍ ውስጥ ያለው የገበያ ድርሻ  50 ከመቶ መሆኑን መረጃው ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጠቅላላ የባንክ ዘርፍ ሀብት ያለው ድርሻ 49ነጥብ1 ከመቶ፣ ከጠቅላላ ብድርና ቦንድ ያለው ድርሻ 51ነጥብ 7 በመቶ፣ ከጠቅላላ ተቀማጭ ያለው ድርሻ 48ነጥብ1 በመቶ መድረሱን ያስረዳል፡፡

እንዲሁም ከባንክ ዘርፍ ካፒታል ያለው ድርሻ 43ነጥብ1 በመቶ መድረሱን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

መካከለኛ ዘርፍ የተመደቡ አምስት ባንኮች ሲሆኑ፣ እነሱም በዘርፉ ያላቸው የገበያ ድርሻ 29 በመቶ  እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ካፒታላቸው ከ10 ቢሊዮን ብር የተሻገሩ ባንኮች አዋሽ፣ ዳሸን፣ አቢሲንያ፣ የኦሮሚያ ኀብረት ሥራ ባንክ፣ ፀደይ ባንክና ንብ ባንክ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ ባንኮች  ‹‹ትንሽ›› ተብለው የተመደቡ ሲሆን፣ በዘርፉ ያላቸው የጋራ የገበያ ድርሻ 22 በመቶ ብቻ መሆኑን መረጃው አስታውቋል፡፡

በመካከለኛና ትንሽ ዘርፍ ስር ያሉት ባንኮች ከብድር፣ ሀብት፣ ተቀማጭ፣ ካፒታልና ተያያዥ አመላካቾች አንፃር ከዘርፉ ያላቸው ጥመርታ እያነሰ መምጣቱን ሪፖርቱ ያትታል፡፡

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክንግድ ባንኮች

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!