እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:16:03 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች

ከእናት የተላከው ደብዳቤ

3 ደቂቃ ንባብ
ከእናት የተላከው ደብዳቤ
የአየር ንብረት ለውጥ የዓለማችን ቁጥር ችግር ነው፡፡የአየር ንብረት ለውጥ ዓይነታቸው ብዙ፤ጉዳታቸውም እስከፊ ነው፡፡አሜሪካዊዋ ለትውልድ መልዕክቷን ያስተላለፈችው ኃላፊነቷን ለመወጣት ነው፡፡ምንም እንኳን፤የእገሯ ምርጥ የአየር ንብረት ምድርን የማያምኑና አገሪቱን ከዓለም አቀፍ መድረኮች ያራቋት ቢሆንም፡፡

ውድ ልጆቼ፤

በአክስታቸሁ ካስይ ሠርግ ላይ በታደምኩበት ወቅት፤ ስልኬ የአደጋ ምልክት አሳየኝ-የአደገኛ ጎርፍ ማስጠንቀቂያ፡፡አካባቢዬን ቃኘሁ-በተራራው አጋማሸ ላይ ነን፡፡ድክምክም ባለች ድንኳን ውስጥ ነን፡፡ተበታትነን ከአጎቶቻችን ጋር እየተጨዋወትን፡፡

አዕምሮዬ እናንተን አሰባስቤ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ሥፍራ መባዝን ጀመረ፡አስፈላጊ ከሆነ፡፡በተግባር ግን ምን ማድረግ እንደምችል ግን አላውቅም ነበር፡፡

 ከጥቂት ቀናት በፊት ወደ ትምህርት ቤት ስወስዳችሁ የፖቶማክ ወንዝ የነበረውን ሙላት ታስታውሳላችሁ፣በዚያኑ ቀን በሜሪላንድ ዌስተርን ፖርት የሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አንደኛውን ፎቅ አጥለቅልቆ 150 ተማሪዎችና መምህራንን እንዳይወጡ ማድረጉንም ሰምታችኋል፡፡የአሰቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች ደርሰውላቸው በጀልባዎች ታግዘው ወስዷቸው ዳኑ ተረፉ እንጂ፡፡

 አሁን ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በክረምት(ሰመር) ካምፕ የነበሩ ልጆች በገጠማቸው ተመሳሳይ አደጋ ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ወላጆቻቸው ኀዘን ላይ ናቸው፡፡

 በዛሬዪቱ ዓለም ወላጆች የገጠመን የተቃረነ እውነታ እንዲህ ዓይነት ነው፡፡

ልጆቻችን እየተቀየረ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ውሰጥ እየኖሩ ነው፡፡ከአማካይ በላይ የዝናብ መጠን፣ከመቶ ዓመታት አንዴ ይመጣ የነበረው ማዕበል ደጋግሞ መከሰት,፣የከፋ ድርቅ፣ ክብረ ወሰን የሚሰብር ሙቀት በመከሰታቸው ዛሬንና ነገን ለመኖር መገደድ ጀምረዋል፡፡ለእኔ ትውልድ እነዚህ ሁሉ ከልክ ያለፉ ናቸው፡፡አማካይ የሚባለውን ያለፉ፡፡ይህንን ዝብርቅርቆሸ እንደ ባህል እየተቀበልነው መጥተናል፡፡

በልጅነቴ አንድሪው የተባለው ማዕበል 11 ዓመት ልጅ ሳለሁና ሁጎ የተሰኘውን ደግሞ ስምንት ዓመት በነበርኩበት ጊዜ ጉዳት ሲያደርሱ አስታውሳለሁ፡፡አኤአ 2017 ወዲህ ሃርቬይ፣ኢያንና ኢዳ የተባሉ ማዕበሎችን በልጅነቴ ካየኋቸው ማዕበሎች በበለጠ ጉዳት ሲያደርሱ ተመልክቻለሁ፡፡ሄለና ማዕበል የካሊፎኒያ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ አውድሟቸዋል፡፡ከዚሀ በፊት ማዕበል እንደማያሰጋቸው ሲገለጹ የነበሩትን ቦታዎች፡፡

 ዓለማችን እየሞቀች በሄደች ቁጥር ርጥበት ባለባቸው ሥፍራዎች በትነት ወደ አየር ውስጥ ይገባል፤አየሩ በውሃ ትነት እየተሞላ በሄደ መጠን ዝናብ በከፍተኛ ደረጃ መጠን ዝናብ እየጣለ፤ይህ ለአጭር ጊዜ የሚጥለው ዝናብ ጎርፍ ያስከትላል፡፡ይህም በቴክሳስ ግዛት የተከሰተውን አደገኛ ጎርፍ ዓይነት በማሰከተል ጉዳት ያደርሳል፡፡

 በቀጣይም በመላው አሜሪካ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል፡፡በመሬትና ከባህር ዳርቻዎች፡፡እኤአ 2023 አንድ ቀን በጣለ ጎርፍ በኒው ዮርክ ከተማ 150 ትምህርት ቤቶች ተጥለቅልቀዋልና፡፡

 እኤአ 2024 ከቀዳሚው ዓመት በበለጠ ሞቃታማ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡በተጨማሪም አሥሩ  ሞቃታማ ዓመታት የተመዘገቡት በዚሁ አሥርት ውስጥ ነበር፡፡በፊላደልፊያ፣ዲትሮትና ሚሊዋኬን በመሰሉ ቦታዎች በነዚህ ’’ሞቃታማ ቀናት’’ ተማሪዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር፡፡

 ይህ ማለት እናንተ በርካታ ጉዳት የሚያስከትሉ የጎርፍ አደጋዎችና ከልክ የሚያልፉ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ የሚመዘገብባቸው ወቅቶች በእኔ ሕይወት ከገጠመኝ  በላይ ወደፊት ይገጥማችኋል፡፡

 እያንዳንዳችሁን ወልጀ በእቅፌ ውስጥ ካደረግኳቸሁ ጊዜ አንሰቶ የወደፊት ሕይወታችሁ የተሳካ፣ ደህንነታቸሁ የተሟላና ደስተኛ እንድትሆኑ ስመኝላችሁ ነበር፡፡አሁን ሳስበው ግን የአየር ንብረት ለውጥ ኑሮአችሁን ያቃውሰዋል ብዬ እጨነቃለሁ፡፡

 አዝናለሁ፡፡እኛ የእኔ ትውልድ እናንተን ለመጠበቅና በቂ ሥራ አልሰራንም፡፡ወይንም እየተቀየረች ባለችው የሚመጥን ተግባር አላከናወንም፡፡ሙቀት ያዘለ ብክለት ወደ አካበቢያችን ማመንጨታችንን ቀጥለናል፡፡በፌዴራል መንግሥቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራት ችግሩን ለማቋቋም የሚያስችሉ አይደሉም፡፡

ብዙዎች በአካባቢያቸው እየሆነ ባለው የሚጨነቁ ቢሆንም፤ሌሎች በርካቶች ምን እየተፈጠረ እንደሆን በቅጡ የተገነዘቡ አይመስሉም፡፡ በጉዳዩ ላይ በምን መልኩ መነጋገር አልቻሉም፤ምን ማድረግ እንዳለባቸውም አላወቁም፡፡

እኔም ከነዚሀ ሰዎች አንዷ ነበርኩኝ፡፡ያ የተቀየረው የአየር ንብረት ለውጥ መረጃ ባገኘሁበት ጊዜ ነው፡፡የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ በአየር ለውጥ ሳቢያ 1ነጥብ 5 ዲግሪ ሙቀት መጨመር እንደሚኖር አወቅኩኝ፡፡ የታላላቅ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች በአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን አውዳሚ ችግሮች ለመከላከል የቀረን ጊዜ 10ዓመታት እንደማይበልጥ አሳውቀውናል፡፡

 ሦስታችሁ ልጆቼ በረንዳው ላይ ስትጫወቱ እየታያቸሁኝ መላ አካላቴ ተሸመደመደ፡፡የነበረኝ የተሳሳተ አስተሳሰብ አናደደኝ፡፡የሩቅ ጊዜ ስላለነበር፡፡ይሄን ቴክኖሎጂ የሚፈታው ችግር አይደለም፡፡ሕይወታችሁ በመሠረታዊነት የሚቀረጸው እየተቀየረ ባለው የአየር ንብረት ነው፡፡እኔ መማርና በጉዳዩ ላይ መሥራት እፈልጋለሁ፡፡

 እኔ የተገነዘበኩት ነገር ቢኖር ሁላችንም የጋራ ዕጣ ፈንታችንን ለመወሰን መጫወት ድርሻችንን መወጣት አለን፡፡ሁሉንም ጥያቄዎች ለመመለስ ባንችል እንኳን፡፡ሰዎችን መርዳት አለብን፡፡በተለይም የእናንተን ትውልድ፡፡ችግሩን አውቆ ወደ ዘላቂ መፍትሔዎች ለመፈለግ፡፡ይህ የምንጀምረው በመነጋገር ነው፡፡የራሳችንን የተሰሳተ አስተሳሰብ ቀይረን በተግባር ለመመንዘር ቆርጠን በመወሰን፡፡

 እንደ ወላጅነቴ በአየር ንብረት ጉዳይ የወጡ ፖሊሲዎችን በማስተዋወቅ የእናንተን ደህንነትና የወደፊት ሕይወታችሁን በመጠበቅና አቅማቸሁን በመገንባት ለውጥ ለማምጣት እሰራለሁ፡፡

 የልጅነት ዘመን ይቀየራል፤የወላጅነት ዘመንም እንደዚሁ ያልፋል፡፡ሁላችንም የምኖርባት ደህንነቷ የተጠበቀ ዓለም ለእናንተና ለቀጣ ለሚሆነው ትውልድ ማውረስ ይጠበቅብናል፡፡

 ፍቅር

እናታችሁ

ደብዳቤው ከታይም መጽሔት ጁን 15/202 5(ሐምሌ 9ቀን 2017)ዕትም የተተረጎመ ነው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥአሜሪካ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!