እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:28:22 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ከዘጠኝ ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል-ቦርዱ

1 ደቂቃ ንባብ
ከዘጠኝ ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል-ቦርዱ
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል፡፡
ዘንድሮ ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ መራጮች  መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤የካቲት 28/2018 በተጀመረው ምዝገባቸውን በማከናወን የመራጭነት ካርዳቸውን በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡

በዚህም የመራጮች ምዝገባ በዲጂታልና በማኑዋል እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።

የመራጮች ምዝገባ ለአንድ ወር ያህል ይካሄዳል፡፡

ለምርጫው የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ስርጭት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተጓጉዙ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ለሚደረገው ምርጫ 11ሺህ የሚደርሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የግል ዕጩዎች ለውድድሩ ቀርበዋል፡፡
የመራጮች ምዝገባምርጫ ቦርድምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!