የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት የአፍሪካውያን ሕይወት እያመሰቃቀለው ነው::
በዓለም ገበያ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 100 ዶላር እየተሸጠ ነው፤ይህም ከአራት ዓመታት በኋላ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ጦርነቱ ነዳጅ ሸማች የሆነቸውን አሀጉር የዋጋ ጭማሪ እንዲገጥማት በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የተቀሰቀሰው ጦርነት የአፍሪካውያን ሕይወት ይነካል፤ የዋጋ ንረትና ኑሮ ውድነት እንዲከሰት በማድረግ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሆርሙዝ ወሽመጥ የዓለም አንደ አምስተኛው ነዳጅ የሚያልፍበት መሥመር በመሆኑ ነዳጅ ወደሚፈልግበት አቅጣጫ እንዳይጓዝ ችግር መፈጠሩን የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
‹‹አፍሪካ ነዳጅ ገዢ በመሆኗ ለዚህ ዓይነት(ጦርነት) ተጋላጭ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ናት፡፡የነዳጅ እጥረት ሲከሰት ዋጋው ይጨምራል፡፡ይህም የአፍሪካ መገበያያ ገንዘቦች መዳከምን ይፈጥራል፡፡ባለሀብቶች ገንዘባቸውን ወደ ዓለም አቀፍ መገበያያዎች በተለይ ወደ ዶላር ቀይረው ያስቀምጣሉ››የሚሉት የዜሮ ካርቦን አናይሊቲክስ ተመራማሪው ኒክ ሂይድሌይ ናቸው፡፡
እነዚህ ሁሉ ችግሮች ተጠረቃቅመው በአፍሪካውያን ሕይወት ላይ ጫና ያሳድራሉ ያሉት ተመራማሪው፣ይህም በተለይ ኢኮኖሚያቸው በወጪ ምርት(ኤክስፖርት)ጥገኛ የሆኑትን እንደ ኬንያና ጋና የመሰሉ አገሮችን ይጎዳሉ ብለዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከአራት ዓመታት በፊት ሲጀመር በነዳጅ ዋጋ ጭማሪና ኢኮኖሚዋን በማዳከም የነዳጅ ዋጋ እስከ 25 በመቶ ጭማሪ እንዲያሳይ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
በቀጣናው የተከሰተው ግጭት አንዳንድ ነዳጅ አምራች አገሮችን ተጠቃሚ ያደረገበት ሁኔታ የፈጠረ ቢሆንም፤በተለይ ነዳጅ ሸማች የአፍሪካ አገሮች ሕይወት ለጉስቁልና መዳረጉን ዘገባው ያመለክታል፡፡
ጭማሪው በተለይ በትራንስፖርት ዘርፍ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን፣የኬንያ፣የዑጋንዳ፣የናይጄሪና የጋና ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዱ እንደሚችሉ መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ አስታውቋል፡፡
አሜሪካና እሥራኤል በኢራን ላይ ባለፈው ሣምንት የከፈቱት ጦርነት አድማሱን ወደ ሌሎች የቀጣናው አገሮች በመስፋፋቱ የነዳጅ ምርት፣ግብይትና ስርጭት ታውኳል፡፡
ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎችና ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ወደ ቀጣናው አገሮች የሚደረጉ በረራዎች ተስተጓጉለዋል፡፡
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!