እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:26:32 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

የመገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ተግባር ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር ነው

2 ደቂቃ ንባብ
የመገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ተግባር ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር ነው
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበርና የልዕልና ጉዞዋን ለዓለም ማስተዋወቅ የመገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ተግባር ሊሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበርና የልዕልና ጉዞዋን ለዓለም ማስተዋወቅ የመገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ተግባር ሊሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበርና የልዕልና ጉዞዋን ለዓለም ማስተዋወቅ የመገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡
1 / 6

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበርና የልዕልና ጉዞዋን ለዓለም ማስተዋወቅ የመገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን "መገናኛ ብዙሃን ለብሔራዊ ጥቅም" በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው አገር አቀፍ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (/) እንደገለጹት፤ መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም፣ ፍላጎት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሚያስተዋውቅ መልኩ አጀንዳዎቻቸውን መቅረጽ አለባቸው፡፡

ብሔራዊ ጥቅምን ማስተዋወቅ ማለት ኢትዮጵያ ለመለወጥ፣ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥና በዓለም መድረክ ተገቢ ስፍራዋን ለመያዝ ያላትን ጽኑ ፍላጎት ማሳየት መሆኑን በማመላከት።

ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል መገናኛ ብዙኃን በአደረጃጀት፣ በይዘት ጥራትና በሰው ኃይል አቅም ራሳቸውን በማዘመን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያረጋግጡም  አስገንዝበዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ የሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (/) እንዳስታወቁት፤ ብሔራዊ ጥቅም ሲከበር የአገርና የሕዝብ ብቻ ሳይሆን፤ የሚዲያ ተቋማትም ጥቅም ይጠበቃል፡፡

በመሆኑም የመገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙያዎች  ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራ አንደሞ መገናኛ ብዙኃን ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ  መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆኑ መረጃ ሰጪዎችም ለአገር ጥቅም ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እንደገለጹት፤ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስረጽ ከመደበኛው የዜና አቀራረብ ባለፈ፤ የመዝናኛ ኢንዱስትሪውን በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ ነው።

እንደ ሆሊውድ ያሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመጥቀስ የታቀደበትና ግልጽ ዓላማ ያለው የጥበብ ሥራ ሕዝብን እያዝናና ቁም ነገር ማስተላለፍ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ተሰሚነትና የዲፕሎማሲ ስኬት ለማሳደግ በውጭ ግንኙነት ዘርፍ ልዩ ዕውቀት ያላቸው ጋዜጠኞች ሚና የማይተካ ነው  ብለዋል።

ወቅታዊ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ሁኔታዎችን በሚገባ የተረዱና አጀንዳ ተኮር የሆኑ ባለሙያዎችን ማፍራት፣ የአገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበርና ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም ለማድረስ ዋነኛው ስትራቴጂካዊ መሣሪያ መሆኑን አመላክተዋል።

መገናኛ ብዙኃንብሔራዊ ጥቅም

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!