እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:50:25 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

የማዕድን ሚኒስቴርን የዲጂታል መሠረተ ልማት ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

1 ደቂቃ ንባብ
የማዕድን ሚኒስቴርን የዲጂታል መሠረተ ልማት ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ
በስምምነቱ መሠረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱንና የተጠሪ ተቋማቱን የደህንነት ካሜራ (CCTV)፣ የዲጂታል መረጃ ማስተላለፊያ (Digital Signage)ና የኔትወርክ መሠረተ ልማት የማሻሻልና የማዘመን ሥራዎችን ያከናውናል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የማዕድን ሚኒስቴርን እና ተጠሪ ተቋማቱን የዲጂታል መሰረተ ልማት ለማዘመን የሚያስችል የሥራ ውል ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል። 

ስምምነቱን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግሥት ሐሚድ እና የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ፈርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱንና የተጠሪ ተቋማቱን የደህንነት ካሜራ (CCTV)፣ የዲጂታል መረጃ ማስተላለፊያ (Digital Signage)ና የኔትወርክ መሠረተ ልማት የማሻሻልና የማዘመን ሥራዎችን  ያከናውናል።

ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ የዲጂታል መሰረተ ልማትን በመገንባትና የወረቀት ግንኙነትን በማስቀረት፣ ለአገር ልማት የጀርባ አጥንት የሆነውን  ተቋም ሥራውን በዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማቀላጠፍ ያስችለዋል። 

አጋርነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክረውም እምነታቸውን ገልጸዋል።

ሚኒሰትሩ ተቋማቸው ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት አስፈላጊውን ዝግጁነት ማድረጉን ጠቁመው፣ ስምምነቱ ሚኒስቴሩ እያከናወነ ባለው የዲጂታላይዜሽን ሽግግር ላይ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።

ስምምነቱን  የተቋማትቱን የሥራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ከመሆኑም ባለፈ፣ ወደፊትም በሳይበር ደህንነትና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመሥራት እንደሚያስችል ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ሚኒስቴሩ ይህንን የቴክኖሎጂ ማሻሻያ ፕሮጀክት ለአስተዳዴ የሰጠው አስተዳደሩ በመረጃ ደህንነትና በቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያለውን አገራዊ ኃላፊነትና የላቀ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑም በመድረኩ ላይ ተገልጿል።


ኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂሳይንስና ቴክኖሎጂ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!