እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:15:54 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ

1 ደቂቃ ንባብ
የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 አራዝሟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 አራዘመ።

የቦርዱ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ከየካቲት 28ቀን 2018ዓ.ም እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያከናውን ማሳወቁ ይታወሳል።ቦርዱ የዕጩዎችና የመራጮች ምዝገባ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማከናወን ባወጣው ዕቅድ መሠረት በአሁኑ ወቅት የዕጩዎችን ምዝገባ አጠናቋል።በጊዜ ሠሌዳው መሠረት የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣በዚህ ሂደት ውስጥ፦

 በተያዘው ዕቅድ መሠረት በተወሰኑ አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የኔት-ዎርክ አቅርቦት እና በምዝገባ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በፍተሻ እየለዩ ሲስተሙን አስተማማኝና ቀልጣፋ ለማድረግ ሂደቱ የጠየቀውን ጊዜ ማካካስ በማስፈለጉ፣

የኔት-ዎርክ አቅርቦታቸው አስተማማኝ ነው ተብለው የቀረቡ የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የኔት-ዎርክ አቅርቦት አለመኖሩ በተጨባጭ በመታየቱ  ወደ ማንዋል በመቀየር ሂደት ለባከነ ጊዜ ማካካሻ በማስፈለጉ እና

በተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ በትራንስፖርት አቅርቦት ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ በወቅቱ ባለመድረሳቸው የተፈጠረውን የመራጮች ምዝገባ መዘግየት ማካካስ አስፈላጊ በመሆኑ ቦርዱ የመራጮችን የምዝገባ ሁለት የበዓል ቀናትን ሳይጨምር  እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018ዓ.ም አራዝሟል።

የመራጮች ምዝገባ መራዘምምርጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!