እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:23:49 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የቤት ውስጥ የዓሣ እርባታ ቴክኖሎጂ ምርትና ምርታማነቱን ያሳድጋል

2 ደቂቃ ንባብ
የቤት ውስጥ የዓሣ እርባታ ቴክኖሎጂ ምርትና ምርታማነቱን ያሳድጋል
Demonstration of Acquaculture
1 / 5

የቤት ውስጥ የዓሣ እርባታ ቴክኖሎጂ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ ሚናው የላቀ መሆኑን ተመላከተ፡፡

የዓሣ እርባታ ጥንታዊ ልምድ መሆኑ የሚታወቅና በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወደ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ላይ የሚገኝ የግብርና ንዑስ ክፍል ነው። 


በተለይም "ሪሰርኩሌቲንግ አኳካልቸር ሲስተም" (RAS) የተባለው ዘመናዊ አሠራር ለዘርፉ እመርታ በማምጣት እየታወቀ መጥቷል። 


ይህ ቴክኖሎጂ በበለጸጉ አገሮችበከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ለንግድ ሥራ ከመዋሉ ባለፈ፥በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች ደግሞ በአነስተኛ ቦታ የሚፈልግ፥ ወጪ ቆጣቢና በቀላሉ ስለሚተገበር ተመራጭነትን አግኝቷል። 


የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ አማካሪ ጽጌረዳ ፍቃዱ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የዓሣ ሀብቷን ለምግብ ዋስትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ለማዋል በቴክኖሎጂ ታግዛ በትኩረት እየሰራች ትገኛለች። 


በዚህም የአልፋ ኢኖቬቲቭ የግብርና ማቀነባበሪያን መሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እስከ አርሶ አደሩ በማድረስ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ሲሉ በአዳማ በተካሄደ ዐውደ ጥናት ላይ ተናግረዋል። 


ይህም የውጭ ምርትን ለመተካት፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠርና የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት  ፋይዳ እንዳለው በማስረዳት። 


የሚኒሰቴሩ የዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ቀደም ሲል ከቤት ውጭ (Out-Door) ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው የዓሣ ዕርባታ በአነስተኛ መሬት በቴክኖሎጂ በመታገዝ በቤት ውስጥ ዓሣ እርባታ (Indoor-Aquaculture) መተግበር እንደጀመረ አስታውቀዋል። 


ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር የአገሪቱን ዓመታዊ የዓሣ ምርትን ለማሳደግ ለተያዘው ግብ መሳካትና የግል ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማስፋት መሠረት  መጣሉን አመልክተዋል፡፡ 


የአልፋ ኢኖቬቲቭ የግብርና ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ  የተወሰነ የግል ማህበር በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከ 3ነጥብ6 እስከ አራት ሚሊዮን የዓሣ ጫጩቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ እያባዛ ነው ሲል የግብርና ሚኒስቴር ያሰራጨው መረጃ ያመለክታል፡፡

Addis Ababa

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!