እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:51:50 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

የተማሪዎች የስፔሊንግ ውድድር በአዲስ አበባ

2 ደቂቃ ንባብ
የተማሪዎች የስፔሊንግ ውድድር በአዲስ አበባ
ስምምነቱ ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን የቃላት ዕውቀታቸውን፣ የማንበብ ባህላቸውን፣ የቃላት አነባበብ ስልታቸውንና በራስ መተማመናቸውን የሚያሳድጉበትን መድረክ ያመቻቻል።

ወጣቱ ትኩስ ኃይል ነው።አገርም በወጣቶች ትገነባለች።

ወጣት ቢማር፣ቢሰራ፣ቢመራመርም ሆነ በሌሎችም ዘርፎች ቢሰማራ ውጤታማ ይሆናል።

አገር ወጣቶቿን ከያዘችና በትክክለኛው መንገድ ከመራቻቸው አትራፊ ናት።

ወጣቱን ትውልድ በሁለንተናዊ መልኩ በአካልና በሥነ ልቡና ቀርጾ አገር ተረካቢ ትውልድ ማድረግ የቤተሰብ፣የማህበረሰብና የመንግሥት ድርሻ አላቸው።

በትምህርት ላይ የሚገኙ ወጣቶች በመማር ማሰተማር ሂደት ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ማድረግም አንዱና የሚደገፍ ተግባር ነው።

ትምህርት ቤቶች ሕፃናትና ወጣቶች ተረክበው በማሰተማር ለትምህርት ተደራሸነትና ጥራትን የሚጫወቱት ሚና የላቀ መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህ አልፎም በትምህርታቸው ጎበዝና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ውደድሮች እንዲካፈሉ ሁኔታዎችን ሲያመቻቹም አእሰየው ያሰኛል።

የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር መፈራረሙ ለዚህ ጥሩ ማሳያ አድርጎ መውሰድ  ይቻላል።

የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥትና የግል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ከቢሮው ጋር ማድረጉን አስታውቋል።

ስምምነቱ  ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን የቃላት ዕውቀታቸውን፣ የማንበብ ባህላቸውን፣ የቃላት አነባበብ ስልታቸውንና በራስ መተማመናቸውን የሚያሳድጉበትን መድረክ ያመቻቻል።

ይህም ፕሮግራሙ በከተማ ደረጃ በተቀናጀ መልኩ እንዲተገበር መንገድ እንደሚከፍት ገልጿል ድርጅቱ።

የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ መስሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዓቢይ ተክሌ እንደተናገሩጹ፣ ስምምነቱ በወረቀት ላይ ከሰፈረ ፊርማ ባለፈ፤ ለልጆች የተገባ ቃል ኪዳን ነው።

በስምምነቱ መሠረት ፕሮግራሙ በትምህርት ቤቶች፣ በመምህራንና በአስተባባሪዎች ትብብር ይተገበራል።

ተማሪዎች በተለያዩ የቃላት ዝርዝሮች፣ የክፍል ውስጥ እንቅስቃሴና በትምህርት ቤት ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም የፈጠራ ሥራ የታከለባቸው ከመደበኛ ትምህርት ውጪ የሆኑ ተግባራት ተወዳዳሪና ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ከሚኖራቸው ሚና አንጻር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጡን በመግለጫው ተመላክቷል።


ወጣቶችትምህርትየተማሪዎች ውደድር

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!