እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:27:30 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:27:30 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
የተሰባጠረ የአመጋገብ ሥርዓት ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት!
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
አንድ ሰው በቀን ውስጥ ስድስቱን የምግብ ምድቦች ማለትም ብዕርና አገዳ/መደበኛ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋፅዖና ቅባት/ዘይት እንዲሁም በአንድ ገበታ ደግሞ አራት የምግብ ምድቦችን አካቶ መመገብ አለበት፡፡
1 / 2
ግብርና ሚኒስቴር ከዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉን የተስባጠረ ምግብ ዝግጅት ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በንድፈ-ሃሳብና በተግባር የታገዘው ስልጠና
የኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ መሆኑን ክሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ስልጠናው በአመጋገብ መመሪያ አተገባበርና ስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርናን መሰረት ያደረገ የምግብ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ለአራት ቀናት የተስጠው ስልጠና የምግብ ደህንነትና ጥራት አጠባበቅን ያካተተ እንደነበርም ገልጿል፡፡
በስልጠናው አንድ ሰው በቀን ውስጥ ስድስቱን የምግብ ምድቦች ማለትም ብዕርና አገዳ/መደበኛ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋፅዖና ቅባት/ዘይት እንዲሁም በአንድ ገበታ ደግሞ አራት የምግብ ምድቦችን አካቶ መመገብ እንዳለበት ተገልጿል፡፡
የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት ሚናው የጎላ መሆኑን እንደተገለጸ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
አንድ ሰው በቀን ውስጥ ስድስቱን የምግብ ምድቦች ማለትም ብዕርና አገዳ/መደበኛ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋፅዖና ቅባት/ዘይት እንዲሁም በአንድ ገበታ ደግሞ አራት የምግብ ምድቦችን አካቶ መመገብ እንዳሉት ተመላክቷል፡፡
ከሚኒስቴሩ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች፤ የሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትና የሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማህበራት ባለሙያዎች ስልጠናውን መከታተላቸው ታውቋል፡፡
የተስባጠረ ምግብ ዝግጅት
ጤና
ግብርና
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!