
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን ዛሬ ጀመረ።
ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ልምምዱን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አድርጓል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለማጣሪያ ጨዋታው ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በልምምዱ ላይ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ለውጭ ክለቦች ከሚጫወቱት ጋቶች ፓኖምና ከነዓን ማርክነህ በቀር ሁሉም ተጫዋቾች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ታደርጋለች።
ቀጣዩን የአፍሪካ ዋንጫ ኬንያ፣ ታንዛንያና ዑጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይስተናገዳል።
አገሮቹ በቅንጅት የሚያዘጋጁት 36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚካሄደው በ2019 ነው።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!