እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:22:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:22:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ስፖርት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
1 / 3
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀ።
ሻምፒዮናው ከመጋቢት 15 -20/2018 በአዲስ አበባ አደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ተካሂዷል።
በሻምፒዮናው ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የሰዓት መመዝገቢያ ማሽን (Time Tronics) ሥራ ላይ ውሏል።
ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ታልሞ ሻምፒዮናው መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ሻምፒዮናውን 36 ክለቦች፣ ተቋማት፣ ዘጠኝ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮችን የወከሉ ከአንድ ሺህ በሚበልጡ ተወዳዳሪዎች ተካፍለውበታል።
ከተወዳዳሪዎቹ 621 ወንዶች ሲሆኑ፤ 436ቱ ደግሞ ሴቶች ነበሩ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል ቀዳሚ በሆነው ሻምፒዮና ማጠቃለያ 10 የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውንበታል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮናው
ን በበላይነት ያጠናቀቀበትን ውጤት አስመዝግቧል።
መቻል ሁለተኛ ሲወጣ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህንና የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ለአሸናፊ ክለቦችና አትሌቶች የገንዘብ፣ ዋንጫዎችንና ሜዳሊያዎችን ሰጥተዋል።
ለሻምፒዮናው 10 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉም በመዝጊያው ሥነ ሥርዓት ላይ ተነግሯል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና
አትሌቲክስ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!