እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:24:56 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

የኢትዮ-ሩሲያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትብብር

2 ደቂቃ ንባብ
የኢትዮ-ሩሲያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትብብር
ውይይቱ ኢትዮጵያ ድህረ ለውጥ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ የምታደርገው ጥረት አካል ሲሆን፣የሩሲያ ኢንዱስትሪያሊስቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

ኢትዮጵያና ሩሲያ ከምዕተ ዓመት በላይ የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።ግንኙነቱ የአገሮቹ የቆዳ ስፋትና ጥበት፣የመሪዎች መለዋወጥና የዘመናት መቀያየር ሲቀያየረው አልታየም።

አገሮቹ  የሚመሩባቸው ርዕዮተ ዓለሞች ቢለያዩ እንኳ ግንኙነታቸውን ሲያጠይመው እምብዛም አልታየም።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ብሪክስ የተሰኘው የአገሮች ስብስብ አባል በመሆናቸው ነባሩንና ጥልቅ መሠረት ያለውን  ወዳጅነታቸውንና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እየረዳቸው ነው።

ሁለቱ አገሮች ለዘመናት የነበራቸው ትብብርና መደጋገፍ ሰፍቶ አሁን የኑክሊየር ኃይል ለሰላማዊ አገልግሎት እስከ ማዋል ባሉ መስኮችም አድጓል።

አገሮቹ በብሪክስ አባል አገሮች የትብብር ማዕቀፍ ሥር በኢንዱስትሪ ዘርፍ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት በዚህ ሣምንት በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄዳቸው ሌላው የግንኙነታቸው ዕድገት ማሳያ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል  በሩሲያ ኢንዱስትሪና ንግድ ምክትል ሚኒስትር አሌክሴይ ግሩዝዴቭ የተመራ ቡድን ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ የሚያደርስ ውይይት አድርገዋል።

አገሮቹ በብሪክስ አባል አገሮች ስብስብ ውስጥ ሆነው የጀመሩት ግንኙነት ራሱን የቻለ ቀጠናዊ የንግድ ማዕከል ለመፍጠር እንደሚረዳቸው ይታመናል።

የዚህ ባለበዙ ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ትኩረቱ የተሻለ አቅም ያላቸው የማምረቻ(ማኑፋከቸሪንግ)ዞኖች በማቋቋም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማሳደግ ነው።

ውይይቱ ከፍተኛ አቅም ያለው ቴክኖሎጂ የሚያሸጋግር ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ለግብርናና ለኢነርጂ ዘርፎች  የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቷል።

ትብብሩ ኢትዮጵያ ለግንባታው መስክ የሚያስፈልጓትን ምርቶች ከውጭ ማስገባትን መንገዶች በመተለም ወጪ በምትቀንስበትና የሩሲያ ኩባንያዎች በአፍሪካ ነፃ ንግድ ገበያ ለመሳተፍ ስትራቴጂያዊ አጋር ከመፍጠርም ጋር ይገናኛል።

የሩሲያ ባለሙያዎች ዘመናዊ መሣሪያዎች ተጠቅመው በፖታሸና ሌሎች ማዕድናት ልማት እገዛ የሚያደርጉበትም መንገድ ሌላው መወያያ ነጥብ ነበረ።

ውይይቱ ኢትዮጵያ ድህረ ለውጥ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ የምታደርገው ጥረት አካል ሲሆን፣የሩሲያ ኢንዱስትሪያሊስቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

ኢትዮጵያ በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች የማምረቻ (ማኑፋክቸሪንግ) ዘርፍ ቀዳሚ መዳረሻ ለመሆንም የሩሲያን ድጋፍ እንደምትሻም ተመላክቷል።የአገሮቹ ትብብር በትምህርትና በቴክኒክ ሥልጠና መስኮች ይደገፋል ተብሏል።

ሁለቱ አገሮች በኢንዱስትሪው ዘርፍ የጀመሩት ትበብር ለሌሎች የብሪክስ አባል አገሮች  ሞዴል ሆኖ እንዲያገለግል መሥራት እንደሚገባም ሚኒስትሮቹ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።









የማምረቻ ኢንዱስትሪየኢትዮ ሩሲያ ትብብርኢንዱስትሪ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!