እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:26:53 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:26:53 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ምርጫ 2018
የዕጩዎች ስምና የመለያ ምልክት አደራደር ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
2 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ሥነ ሥርዓቱ የዕጩዎችና የፓርቲዎችን ስም፣ ምልክትና ምስል በመራጮች ድምፅ የሚወሰንበት ሥርዓት በመደንገግ የምርጫ ሂደቱን ግልጽ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ መሆኑን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ ነው
1 / 2
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የስምና የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ።
የዕጩዎችና የፓርቲዎችን ስም፣ ምልክትና ምስል በመራጮች ድምፅ የሚወሰንበት ሥርዓት በመደንገግ የምርጫ ሂደቱን ግልጽ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተመላክቷል።
የድምፅ መስጫ ወረቀት የዕጩዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም መለያ ምልክትና የዕጩዎችን ምስል በመያዝ ታትሞ የተዘጋጀና መራጮች ለሚፈልጉት ዕጩ ድምፅ የሚሰጡበት ወረቀት መሆኑም በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደተናገሩት፥ ቦርዱ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተጠናከረ መልኩ ዝግጅት እያደረገ ነው።
በአሁኑ ወቅት የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን፣ እስካሁን ከ18 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
ምዝገባው በዲጂታልና በማኑዋል በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ የሲስተምና የኔትወርክ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ምዝገባው በማኑዋል እንዲካሄድ መደረጉን አስረድተዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች ምዝገባ ተጠናቅቆ በምርጫ ክልሎች የዕጩዎች ስም ዝርዝር በይፋ መለጠፉን ገልጸው፣ለሚቀርቡ ቅሬታዎችም ምላሽ እየተሰጠ ነው ብለዋል።
በአገሪቱ በተቋቋሙ 47ሺህ በሚጠጉ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውንም ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።
ቦርዱ 30 በመቶ የሚሆነውን የመንግሥት የመጀመሪያ ድጋፍ በምርጫወ ለሚሳተፉ ፓርቲዎች መልቀቁንም አስታውቀዋል።
ቦርዱ ከሲቪክ ማህበራት፣ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃንና ጸጥታ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በቦርዱ ከተመዘገቡ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 ዕጩዎች ለምርጫው መቅረባቸውን መረጃዎች ያመለከታሉ።
ከነዚህም 2 ሺህ 98 ዕጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ለማግኘት የሚወዳደሩ ናቸው።
እንዲሁም 8 ሺህ 736 ደግሞ ለክልል ምክር ቤት አባልነት ወንበር ለማግኘት ይወዳደራሉ።
ግንቦት 24/2018 ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር 73 የግል ዕጩዎች ደግሞ መመዘገባቸውም ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ምርጫ
ምርጫ 2018
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!