ማክሰኞ 19 ሜይ 2026
11:52:53 ጥዋት UTC+3 - Addis Ababa
ማህበራዊ

የዲግሪ ሰርተፊኬት ኅትመት -በአንድ ማዕከል ብቻ

2 ደቂቃ ንባብ
የዲግሪ ሰርተፊኬት ኅትመት -በአንድ ማዕከል ብቻ
ኀትመቱ በዚህ ዓመት እንደሚጀምርና ሰርተፊኬቱ የደህንነት መለያ መስፈርቶች የሚያሟላ ሲሆን፣ ልዩ መለያ ኮድ(QR Code) ሴሪያል ቁጥርን ጨምሮ ሌሎች መለያዎችን ያካትታል።
በፌዴራል  መንግሥት ከ160 በላይ ተቋማት ላይ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ አንስተው፤ በቀጣይ በክልሎችና በግል ዘርፍ ሥራው እንደሚቀጥል የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ይሄ ዛሬ የሚሰራውና በቅርቡ እየተከናወነ ያለው የሐሰት ትምህርት ማሰረጃዎችን ለማጥራት በመካሄድ የሚገኝ እርምጃ ነው።

ለዘመናት በአገሪቱ በተሰጡት የሐሰት ትምህርት ማሰረጃዎች በማይገባቸውና በሌላቸው የትምህርት ማስረጃ ያለ አግባበ የተጠቀሙ፣የሚጠቀምባቸውን አገልግሎት ያልሰጡና ሕዝብን የበደሉ ነበሩ።

በያለበት እየተመረቱ ሲታደሉ ከነበሩት ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች መካከል ዲግሪ ይገኝበታል።ሚኒስቴሩ ችግሩን ለመፍታት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ኅትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

 በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ አሰራሩ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለመከላከል ያለመ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጨረታ ባሸነፈ ድርጅት በኩል የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ የሚያሳትሙበት አሰራር ለሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጋላጭ ሆኖ ቆይቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የመንግሥትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸውን ዲግሪ በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲያሳትሙ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

ሚኒስቴሩ አዲሱ ዲግሪ ታትሞ እስኪደርስ ድረስ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚጽፍ  መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

ኀትመቱ በዚህ ዓመት እንደሚጀምርና ሰርተፊኬቱ የደህንነት መለያ መስፈርቶች የሚያሟላ ሲሆን፣ ልዩ መለያ ኮድ(QR Code) ሴሪያል ቁጥርን ጨምሮ ሌሎች መለያዎችን  ያካትታል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የተመረቁ ተማሪዎችን ጨምሮ ከዚህ በኋላ የሚመረቁትም ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ሥርዓት መሰረት በአንድ ማዕከል የሚታተመውን ዲግሪ ብቻ እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ከ2017 በፊት ተመርቀው  ዲግሪያቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአዲሱ አሰራር ብቻ እንደሚስተናገዱ አመልክተዋል።

ከዚህ በፊት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ (Temporary Degree) አሰጣጥ በነበረበት እንደሚቀጥል በማመላከት።


ትምህርትከፍተኛ ትምህርትሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!