እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:15:55 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:15:55 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ሕግና ፍትሕ
ያለደረሰኝ ሽያጭ የፈፀሙ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ኦፕሬሽኖቹ በመኪና መለዋወጫ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግንባታ ግብዓቶች፣ በሥጋ ቤቶች፣ በአልባሳት እንዲሁም በወለል ምንጣፍ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ መካሄዳቸውን አመልክቷል፡፡
ያለደረሰኝ ሽያጭ የፈፀሙ 55 ግብር ከፋዮች ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ከስድስት ወራት የሚደርስ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነባቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እንዳስረዳው ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት በማስፈን ለከተማዋ ልማት የሚውል ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ያለደረሰኝ ሽያጭ በሚያከናውኑ ነጋዴዎች ላይ ተከታታይ ኦፕሬሽኖች ሲያከናውን ቆይቷል።
በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በተካሄዱ ኦፕሬሽኖች በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ 294 ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጿል።
ኦፕሬሽኖቹ በመኪና መለዋወጫ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግንባታ ግብዓቶች፣ በሥጋ ቤቶች፣ በአልባሳት እንዲሁም በወለል ምንጣፍ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ መካሄዳ ቸውን አመልክቷል፡፡
በዚህም ከተጠርጣሪዎች መካከል 55ቱ ጉዳያቸው ለፍርድ ቤት ቀርቦ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን፥ ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ከስድስት ወራት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
ግለሰቦቹ የመንግሥትን ጥቅም ለማሳጣት ከታክስ አስተዳደር ዓዋጅ በተፃረረ መልኩ ያለደረሰኝ ሽያጭ በመፈፀም ወንጀል መፈጸማቸው ተገልጿል።
የተቀሩት 239 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ በቀጣይም ያለደረሰኝ ግብይትና የግብር ስወራን ለመከላከል የሚከናወነው ተግባር እንደሚያጠናክር አስታውቋል።
ሕግና ፍትሕ
ወንጀል
ቅጣት
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!