እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:14:57 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:14:57 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ማህበራዊ
ገነት ፡- ሴቶችን በማብቃት የወደፊት ሕይወታቸውን ማሳያ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
2 ደቂቃ ንባብ
•
AI
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የሸራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ታታሪዋ ገነት ፍሥሐ ባለትዳርና የአንድ ልጅ እናት ነች።
ለዓመታት በአንድ ሄክታር መሬቷ ላይ ጤፍን ታመርታለች። የጤፍ እርሻዋ ምርት ዝቅተኛ ነበር፡፡ ይህም ተስፋ እንድትቆርጥ አድርጓት ግብርና የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ መሆኑን እንድትጠይቅ አድርጎት ነበር።
ከአምስት ዓመታት በፊት ገነት 400 የአቮካዶ ችግኞችን ይዛ "ሁንዳኦል አቮካዶ" ክላስተር ስትቀላቀል ሁሉም ነገር ተለወጠ።
መጀመሪያ ላይ አቮካዶ ምርት ለማግኘት ሦስት ዓመታት እንደሚፈጅ ሲነገራት ተጠራጥራ ነበር ይላል የግብርና ሚኒስቴር መረጃ።
ነገር ግን ከእርሷ በፊት ክላስተሩን የተቀላቀሉ አርሶ አደሮችን ለውጥ በማየቷ ድፍረት ሰጣት።
ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የስልጠናና ማበረታቻ ድጋፍ አግኝታለች። ክላስተር እርሻ በጋራ መሥራትን፣ ግብይትን፣ ሙያዊ ክትትልንና የአቻ ትምህርትን በአርሶ አደሮች ዘንድ አስተዋውቋታል፡፡ ይህም ጥርጣሬን ወደ ዕ
ድል ቀይሯል፡፡
ገነት የአቮካዶ ማሳዋን ለመንከባከብ ባዮጋዝ እና ቫርሚኮምፖስት በመጠቀም ዘላቂ የግብርና ልምዶችን ትተገብራለች። በአቮካዶ ተክሎች መካከል ጎመንን በመትከል ገቢዋን ታሳድጋለች።
ባለፈው ዓመት ትዕግስትዋ ፍሬ አፍርቶ 12 ኩንታል አቮካዶ በመሰብሰብ 135ሺህ ብር ገቢ አግኝታለች።
ሥራዋንም በማስፋትም ከ20 ዶሮ እርባታ ወደ 1 ሺህ 500 የእንቁላል ጫጩት እርባታ ተሸጋግራለች። አንድ የወተት ላምም ገዝታ በየቀኑ 10 ሊትር ወተት ታልባለች፡፡ አንድ ሊትር በ70 ብር በመሸጥ በወር 21 ሺህብር ተጨማሪ ገቢ ታገኛለች።
የአርሶ አደር ገነት ለውጥ ለብዙዎች ምሳሌ ነው። ገነት አሁን ልጇን በግል ትምህርት ቤት ታስተምራለች፡፡
ሰባት የቀንድ ከብቶችም ታደልባለች፣ ዘመናዊ ቤት ገንብታለች።
ገነት አሁን ያላት ጠቅላላ ሀብት 10 ሚሊዮን ብር በላይ ይገመታል። የወደፊት ዕቅዷ ለአቮካዶ እርሻዋ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ ፓምፕ መግዛትና በሞጆ ከተማ ቤት መገንባት ነው።
በአንድ ወቅት በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ዱባይ ከተማ ለስድስት ዓመታት ስለኖረች፣ የእርሻ ሥራዋን ትታ መሄድ አስባ ነበር። ነገር ግን የክላስተር እርሻ በአገሯ ላይ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ስላሳመናት እንድትቆይ ምክንያት ሆናት፡፡
“የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አርሶ አደሩሯን ከወደቀበት አንስቷታል፣ ሥልጠናም ሰጥቷታል። በሕይወታችን ውስጥ ለለውጥ መሠረት ሆኗል። ሴት አርሶ አደሮች ከወንዶች እኩል መስራት አለባቸው፤ ይህ ከሆነ ብቻ ነው ለውጥ ማምጣት የሚቻለው” በማለት ገነት መልዕክቷ በግልጽ ትናገራለች።
ምርታማነቱ ዝቅተኛ ከነበረው የጤፍ እርሻ ወደ አቮካዶ የክላስተር እርሻ የተሸጋገረው
የአርሶ አደር ገነት ታሪክ የጥንካሬ፣ ፈጠራና በጋራ የመሥራት ኃይል ምስክር ነው።
ኢኮኖሚ
ወጣቶች
ሕግ ማስከበር
ሥራ ፈጠራ
ግብርና
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!