እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
08:28:15 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ስፖርት

ጎልፍ በአዲስ ምዕራፍ-በመከላከያ

1 ደቂቃ ንባብ
 ጎልፍ በአዲስ ምዕራፍ-በመከላከያ
በአምስት ምድቦች ተከፋፍለው ወደ ሜዳ የገቡት 16 ምርጥ ሴት ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ተቋማትና ከዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የተውጣጡ ናቸው።
1 / 2
በኢትዮጵያ የጎልፍ ስፖርት ታሪክ ውስጥ አዲስ የታሪክ ገጽ ተገልጧል። 

የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የሴቶች የጎልፍ ውድድር አረንጓዴው ሜዳ ላይ ለየት ያለ ውድድር አዘጋጅቷል። 

ውድድሩ ስፖርታዊ ፉክክር ብቻ ሳይሆን፤ የሴቶችን ጥንካሬ፣ ሥልጣኔና አዲስ ራዕይን ያሳየ መድረክም ነበር።

በአምስት ምድቦች ተከፋፍለው ወደ ሜዳ የገቡት 16 ምርጥ ሴት ተወዳዳሪዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ተቋማትና ከዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የተውጣጡ ናቸወ።

በዚህ ውድድር ደግሞ ብርቱ ፉክክር በማድረግ የጽናት ተምሳሌት ሆነው የታዩት የመከላከያ ቅርስና ሙዚየም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ጥሩዬ አሰፌ ይባላሉ።

ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ በውድድሩ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበሩ ሲሆን፣ ስፖርቱ ለጤና ብቻ ሳይሆን ለአገርም የገቢ ምንጭ መሆን የሚችል ዘርፍ ነው ብለዋል።

ስፖርቱ በሰዎች መካከል ያለውን ዝምድና የሚያጠናክር የዲፕሎማሲ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑንም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ብቸኛውና ደረጃውን የጠበቀ የጎልፍ መጫወቻ ሜዳ በአገር መከላከያ ተቋም ውስጥ መገኘቱ ደግሞ ተቋሙ ለስፖርቱ እድገትና ለጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ይህ የመጀመሪያው የሴቶች የጎልፍ ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ለስፖርቱ አፍቃሪ ያስተዋወቀችበት መድረክ እንደነበር የአገር መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ይገልጻል።

 ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬና መሰል ጠንካራ ሴቶች ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ አዲስ መንገድ ቀዳጆች ሆነዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት ጎልፍ ክለብ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ያስታወሱት ጄኔራል መኮንኗ፣ተቋሙ ባመቻቸው በዚህ ዕድል በመጠቀም ሁሉም ስፖርቱን የሕይወቱ አካል እንዲያደርገው ጥሪ አስተላልፈዋል።


ስፖርትመከላከያ ሠራዊትጎልፍ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!