እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:42:19 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ለምርጫው ከ42 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዘገቡ

1 ደቂቃ ንባብ
ለምርጫው ከ42 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዘገቡ
ለምርጫው ከተመዘገቡት ውስጥ የወንዶች ቀጥር ከሴቶች ብልጫ በማሳየት ላይ ነው።
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ42 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ለምርጫው ከተመዘገቡት ውስጥ የወንዶች ቀጥር ከሴቶች ብልጫ በማሳየት ላይ ነው።

ይህም ባለፉት ሣምንታት በተመዘገቡ ጠቅላላ መራጮችና በአካል ጉዳተኛ መራጮች ቁጥር በግልጽ ተንፀባርቋል።

ቦርዱ ዛሬ ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2018  ድረስ ባለው ጊዜ 42ሚሊዮን167ሺህ 911 የምርጫ ካርዳቸውን ወስደዋል። 

ከጠቅላላ ተመዝጋቢዎቹ ውስጥ 22ሚሊዮን746ሺህ 79 ወንዶች፣ 19ሚሊዮን 421ሺህ 832 ደግሞ ሴት መራጮች መሆናቸው ተገልጿል።

ቦርዱ  አካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ በተመለከተም በሰጠው መረጃ 96ሺህ274 ወንዶችና 67ሺህ 978 ሴቶች በምርጫው ለመሳተፍ  ለምርጫው ተመዝግበዋል።

ቦርዱ በዚህ ሣምንት ያወጣው የመራጮች ቁጥር ባለፈው ሣምንት ከተመዘገቡት በ5ሚሊዮን195ሺህ930ብልጫ አሳይቷል።

ከዚህም ውስጥ በወንዶች የ2ሚሊዮን 623ሺህ752 መራጮች፣በሴቶቸ ደግሞ የ2ሚሊዮን 572ሺህ 168 ታይቷል።

ለምርጫው ከተመዘገቡት አካል ጉዳተኛ መራጮች በወንዶች የ19ሺህ609ብልጫ ሲታይ፣በሣምንቱ ሪፖርት በሴት አካል ጉዳተኞች የተመዘገበው 4ሺህ 473ነው።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ይካሄዳል።


ምርጫየመራጮች ምዝገባምርጫ 2018

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!