
በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ36ነጥብ 9ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ቦርዱ ማምሻውን ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው ለምርጫ 2018 እስከ ትናንት ድረስ 36ሚሊዮን 971ሺህ 981የመራጭነት ካርድ ወስደዋል።
ከነዚህም 20ነጥብ 1ሚሊዮን የሚሆኑት ወንዶች፤ 16ነጥብ 8ሚሊዮን ደግሞ ሴቶች ናቸው።
ከጠቅላላዎቹ መራጮች መካከልም 72ሺህ 609ወንዶችና 72ሺህ 451ሴቶች አካል ጉዳተኞቸ መሆናቸውን መግለጫው አመላክቷል።
ለምርጫው የተመዘገቡ ጠቅላላ መራጮች ቁጥር ከአንድ ሣምንት በፊት ከነበረበት በ8ነጥብ 6ሚሊዮን ብልጫ አሳይቷል።
ከዚህም የወንድ መራጮች ቁጥር በ4ነጥብ 8ሚሊዮን፤የሴት መራጮች ቁጥር ደግሞ በ3ነጥብ 8ሚሊዮን ዕድገት አሳይቷል።
በአገሪቱ ለምርጫው የተቋቋሙ ከ46ሺህ በላይ ምርጫ ጣቢያዎችና ከ187ሺህ በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎች በሥራ ላይ መሆናቸውን ቦርዱ ከዚህ ቀደም ባወጣው መረጃ መግለጹ ይታወሳል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!