እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
05:11:34 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምርጫ 2018

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ28ነጥብ 3ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል

1 ደቂቃ ንባብ
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ28ነጥብ 3ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ28ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች ተመዝግበዋል።የመራጮቹ ቁጥር በስምንት ቀናት ውስጥ የ9ነጥብ 8ሚሊዮን ብልጫ አሳይቷል።
በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ28ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች ተመዝግበዋል።

በምርጫው ለሚወዳደሩ 50 የፖለቲካ ፓርቲዎች ነጻ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምዶች መመደቡም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እንደሚያሳየው ግንቦት 24 ቀን 2018 ለሚደረገው ምርጫ 28 ሚሊዮን 365ሺህ 310 መራጮች ምዝገባቸውን አከናውነዋል።

ለምርጫው እስከ ትናንት የተመዘገቡት 15 ሚሊዮን 317ሺህ ወንዶች ሲሆኑ፣13ሚሊዮን 47ሺህ 698ደግሞ ሴቶች ናቸው።

የመራጮቹ ቁጥር በስምንት ቀናት ውስጥ በ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብልጫ አሳይቷል።

ይህም ከፆታ አንጻር ሲታይ በወንዶች የ5 ነጥብ 1 ሚሊዮን፤በሴቶች የ4ነጥብ 6 ሚሊዮን መራጮች ቁጥር ብልጫ አለው።

ቦርዱ በማኑዋልና በዲጂታል መንገዶች እያከናወነ ያለው የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 የተጀመረ ሲሆን፤ምዝገባውን ለማጠናቀቅ የቀሩት ዘጠኝ ቀናት ናቸው።

ቦርዱ ባለፈው ሣምንት ይፋ ባደረገው መረጃ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ያለው በ46ሺህ 757 ምርጫ ጣቢያዎች መሆኑን አስታውቆ ነበር።

በዚያው መረጃም ከ187ሺህ በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎችን ማሰማራቱን ገልጿል።
 
ቦርዱ በመጪው ምርጫ የሚሳተፉ 50 የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በነጻ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምዶች እንደተመደበላቸው ዛሬ የለቀቀው መረጃ ያሳያል።

ፓርቲዎቹ  ድልድሉ የተደረገላቸው 24 የሬዲዮና 20 የቴሌቭዥን ጣቢያዎችንና ስድስት ጋዜጦችን ተጠቅመው የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ነው።

ቦርዱ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን ከሚያደርጉት የምርጫ ክርክር በተጨማሪ ትናንት በራሱ ማከራከር መጀመሩ መዘገቡ ይታወሳል።


የመራጮች ምዝገባምርጫ 2018ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!