እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:42:36 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ምናሌ ክፈት
የሀገር ውስጥ
ዓለም አቀፍ
ዲያስፖራ
እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
03:42:36 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ወቅታዊ ጽሁፎች
ፖለቲካና ዲፕሎማሲ
ማህበራዊ
ባህልና ኪነ-ጥበባት
ምርጫ 2018
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
ኢኮኖሚ
ስፖርት
ሕግና ፍትሕ
የአርታዒዎች ምርጫ
ማህበራዊ
ለወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠረው የግብርና ኢንተርፕራይዝ
በ
ብርሃኑ ተሰማ
•
•
1 ደቂቃ ንባብ
•
AI
ይህ 214 ሥራ አጥ ወጣቶችን ያደራጀ ተቋም ፎሶሊያ፣ አተርና ብሮክሊን በማልማት ላይ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል።
1 / 2
በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክፍለ ከተማ በኪሌሎ ወረዳ ባለፈው ዓመት ነው የተመሠረተው።
ስሙ የቡራ ባሩ የመስኖ ሥራ ኢንተርፕራይዝ ይባላል።
ይህ 214 ሥራ አጥ ወጣቶችን ያደራጀ ተቋም
ፎሶሊያ፣ አተርና ብሮክሊን በማልማት ላይ ነው፡፡
ኢንተርፕራይዙ ባለፈው ዓመት በ43 ሄክታር መሬት ላይ ከአንድ ሺህ ኩንታል በላይ ፎሶሊያ፣ 2ሺህ395 ኩንታል አተርና 877 ኩንታል ብሮክሊን አምርቷል።
በልማቱም 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ማትረፍ ችሏል ይላል የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ፡፡
ምርቱን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት ባለፈ፤ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገተ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ከአባላቱ ባለፈ በአጨዳ ወቅት 500 ለሚሆኑ ሰዎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአንድ ሰው በቀን እስከ 500 ብር ይከፍላል፡፡
መንግሥት ለኢንተርፕራይዙ 78 ሄክታር መሬት በመስጠት፣ ለመስኖ አገልግሎት የሚውል ውሃ በማውጣት፣ ለምርቱ የገበያ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡
የኢንተርፕራይዙ ሊቀመንበር ወጣት አባይ ታደሰ በሕንፃ ኤሌክትሪክ ዝርጋታ ሙያ በዲፕሎማ ተመርቆ ለሰድስት ዓመታት ሥራ አጥ ሆኖ እንደቆየ ያስታውሳል፡፡
ሥራ አጥ ወጣቶች ቅጥርን ከመጠበቅ ይልቅ ተደራጅተው በግብርና ልማት ላይ ቢሰማሩ የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙም መክሯል፡፡
ይሄን ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቤተሰቡን በአግባቡ ማስተዳደር ይቸግረው እንደነበር ገልጾ ፣ በአሁኑ ወቅት በወር ስምንት ሺህ ብር ደሞዝ እያገኘ ኑሮውን በመምራት ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በቀጣይም ኢንተርፕራዙን በማጠናከር ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራ መሆኑንም ሊቀመንበሩ አመላክቷል፡፡
ኢኮኖሚ
ወጣቶች
ሥራ ፈጠራ
ግብርና
0
አወድ
0
አስቀምጥ
አስቀምጥ
አጋራ
አጋራ
0 አስተያየቶች
አስተያየት ይላኩ
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!