እሑድ 19 ኤፕሪል 2026
06:46:21 ከሰዓት UTC+3 - Addis Ababa
ኢኮኖሚ

ለዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያና ፔትሮኬሚካል ፋብሪካ የ2ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር ፀደቀ

1 ደቂቃ ንባብ
ለዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያና ፔትሮኬሚካል ፋብሪካ የ2ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር ፀደቀ
አሊኮ ዳንጎቴ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ድርሻ እየተጫወቱ ያሉት አፍሪኤግዚምን ከመሰሉ ባንኮች ተበድረው በመሥራት ጭምር ነው።

የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት (አፍሪኤግዚም)ባንክ ለዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያና ፔትሮኬሚካል ፋብሪካ ለሚውል የ2ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር ብድር  አፀደቀ ።

ባንኩን ዛሬ ብድሩን ያፀደቀወ ለድርጅቱ  ለመስጠት ካቀደው  አራት ቢሊዮን ዶላር ብድር ውስጥ መሆኑን ገልጿል።

ለአምስት ዓመታት የሚቆየው የብድር ስምምነት በቀን 650ሺህ በርሜል የሚያጣራውን ፋብሪካ አቅም ሉማጠናከር ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል።

ብድሩ  በአፍሪካ ግዙፍ ለሆነው የዳንጎቴ ነዳጅ  ማጣሪያ የገንዘብና የአፈጻጸም አቅሙን  ለማሳደግ  ፋይዳው  የላቀ መሆኑነ ዛሬ ካይሮ፣ግብፅ ውስጥ በተከናወነው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ ተመላክቷል ።

የባንኩ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ(ዶ/ር)በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፣ ባንኩ  ባለፉት 11ዓመታት  ጀምሮ ለዳንጎቴ ቢዝነስ ግሩፕ 15 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብድር ሰጥቷል።

በዚህም  አፍሪካ በነዳጅ ምርቶች ራሷን እንድትችል መርዳቱንና የአፍሪካ እርስ በርስ ውስጥ የንግድ ልውውጥ እንዲጎለብት ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

ይህንንም ያደረገው  ለዓላማዎቹ መሳካት ካለው ቁርጠኝነት በመነጨ ስሜት መሆኑንም በማመላከት።

ስምምነቱ አፍሪካ በነዳጅ ምርቶች ላይ ያላትን የውጭ ጥገኝነት በመቀነስ የአህጉሪቱን አቀፍ የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ ሚና እንደሚኖረውም ተገልጿል።

የዳንጎቴ ኩባንያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ለድርጅቱ የተሰጠው ብድር ድርጅቱን ከአፍሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንደሚያደርገው ገልጸው፣ከዚያም ባሻገር አህጉሪቱ በነዳጅ ምርቶች ራሷን ለመቻል በምታደረገው ጥረት አጋዥ ነው ብለዋል።

ኢኮኖሚብድርየዳንጎቶ ግሩፕ

0 አስተያየቶች

ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!