
የቢሮው ኃላፊ ቤተልሔም ዳንኤል በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ የፍትህ ዘርፍ ትራንፎርሜሽን እቅድ ተዘጋጅቶ ከ2016 ጀምሮ በመተግበር ላይ ይገኛል።
እቅዱ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለው ጠንካራ ተቋም በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።
የፍትሕ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ጊዜንና ጉልበትን የቆጠበ ከአድልዖ፣ ከጉቦ፣ ከሙስናና ሌሎች የሥነ-ምግባር ጉድለቶች የጸዳና በቅንነት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በትራንስፎርሜሽኑ የተካተቱ 10 አምዶችን ተግባራዊ ለማድረግ የኀብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ማሳደግና ውጤታማ የኅብረተሰብ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚዲያ ተቋማት ሚና ወሳኝና የጎላ ነው ብለዋል።
የዘርፉ ሥራዎች ወደ ኀብረተሰቡ እንዲደርሱ በማድረግ ሕግ አክባሪ፣ መብቱን የሚያውቅና ግዴታውን የሚወጣ የነቃ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ከፍተኛ ኃላፊነት አንዳለባቸው በማስገንዘብ።
የፍትሕ ተደራሽነትና አማራጭ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም አለመግባባቶችን በባህላዊ መንገድ ለመፍታት በ605 ቀበሌዎች ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ መጀመራቸውን ኃላፊዋ ተናግረዋል።
ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ከመጠቀም አንፃር የግንዛቤ ችግር መኖሩን አንስተው፣በዚህ ረገድ የሚዲያ ተቋማት ኅብረተሰቡን በማስተማር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወልደማርያም በዛብህ (ዶ/ር) የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በሕግና ፍትሕ ዙሪያ የሕዝቡ ግንዛቤ እንዲሰፋና እንዲሰርጽ መሥራት አለባቸው ብለዋል።
ከዚህ አኳያ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በክልሉ በሚገኙ ቋንቋዎች መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ላይ በትኩረትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ በማመላከት።
በመድረኩ የፍትሕ አካላት፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
0 አስተያየቶች
ገና አስተያየት የለም። የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ ይሁኑ!